አዲስ ስራ ከመቀያራችሁ በፊት ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለባችሁ 6 ነገሮች






አዲስ ስራ ከመቀያራችሁ በፊት ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ያለባችሁ 6 ነገሮች
ሁሉም ስራ ሂደት ነው፡፡ብዙ ጊዜ ስራ ቀያየርንም በአንድ ቦታም ለብዙ ጊዜ ቆየን በሙያችን ምን አገኘን ከሚለው ጥያቄ ጋር ቀን በቀን እንፋጠጣለን፡፡ልንቆጣጠረው የማንችለው ነው፡፡በትንሹም ቢሆን በስራዬ ደስተኛ ስለሆንኩ ሌሎች እንዴት ውጤታማ እንደሆንኩ ይጠይቁኛል፡፡ሰዎች ቀን በቀን ስራ መቀየር አለብኝ ወይስ ባለሁበት መሆን አለብኝ አልያም ሙሉ ለሙሉ ሙያዬን መቀየር አለብኝ በሚለው ሀሳብ ውስጥ በየጊዜው ይዋኛሉ፡፡ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ሙልት ያለ መልስ ማግኘት ይከብዳል፡፡ነገር ግን የስራ መቀየር ወይም ባሉበት መቆየት አልያም ደግሞ የሙያ መቀየር ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት ለዚህ የሚረዱንን ስደስት ነገሮች እንመልከት፡፡
1.  ሽሽትን ማስወገድ
ብዙውን ጊዜ የስራ ቅያሬ ከሽሽት የሚነጭ ነው፡፡የምንጠላው ሃላፊን ፣የምንጠላው መስርያ ቤትን አልያም ደግሞ የምንጠላቸውን ያሰለቹንን የስራ ባለደረቦች ሽሽት፡፡አንድ ጊዜ የወደዳችሁት ስራ አልያም ደግሞ የጠላችሁትን ለመለየት ሲያስቸግራችሁ ይችላለል፡፡አንዱ በመልካም ጎኑ አንዱን ደግሞ አማራጭ በማጣት፡፡ነገር ግን ስራ ስትቀይሩም ሆነ ሙያ ስትለውጡ ካላችሁበት መጥፎ ሁኔታ ለመሸሽ ሳይሆን በመትወዱት ስራ ለመለወጥ አስባችሁ መሆን አለበት፡፡መጥፎ አለቃን ሽሽት የትም አትደርሱም፡፡መጥፎ የስራ ጓደኛን ሽሽትም እንደዚያው በየቦታው መጥፎ አለቆች መጥፎ የስራ ባለደረቦች አሉና፡፡ስለዚህ መሆን ያለበት የተሻለና ተሰጥኦችህን ልታሳድጉ የምትችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው ስራ ወይም ሙያ መቀየር ያለባችሁ፡፡

2.  ጥንቅቅ ያለለት ነገር አትጠብቁ
የተሻለን እንጂ ሙሉ ለሙሉ የተዋጣለት ነገርን አትጠብቁ፡፡ምክንያቱም በስራ ፍለጋ ወቅት የምንፈልገውን ነገር የሚያሟላልንን ብቻ ፍለጋ ውስጥ ሰለምንዳክር በቀላሉ ተስፋ እንቆርጣለን፡፡ያለቀለት፣ ሁሉም ነገር የተሟላለት፣ ደሞዙ ጥሩ የሆነ፣ ጥሩ አለቃ ያለበት፣ ምርጥ የስራ ባለደረቦች ያሉበት፣ የትምህርት እድል የሚሰጥ ወዘተ እያልን መድከም የለብንም፡፡ እንደዚህ አይነት የተሟላ ፓኬጅ ያለው መስርያ ቤት በአለማችን ላይ እንደው የለም ማለት ባይቻልም አለ ለማለትም ይከብዳል፡፡ስለዚህ ደምወዙ ጥሩ ከሆነ የስራ አለቃ መጥፎ ቢሆን የማቻቻል፣ የስራ ባለደረቦች መጥፎ ሆነው የቅርብ አለቃችን መልካም ሊሆን የሚችልበትን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ አካሄድ እና ምርጫ ልናስቀምጥ ይገባናል፡፡


 


3.  መቀጠል
እስካላችሁበት ጊዜ ድረስ ያላችሁበትን ስራ ተጠንቅቃችሁ መስራት ይገባል፡፡በትልቅ በትንሹም ስላኮረፋችሁ ወይም ስለተጣላችሁ ወይም የደምወዝ ሁኔታው ስላላማራችሁ እየሰራችሁ ያላችሁትን ስራ መበደል የለባችሁም፡፡ብዙውን ጊዜ ስራ መቀየር ስትፈልጉ የሚመጣው ምክር መክሊትህን ተከተል የሚል ነው፡፡መክሊታቸውን ላላወቁ ሰዎች ይህ አደናጋሪ ነው የሚሆነው፡፡ስለዚህም መጀመርያ ተስጥኦን መለየት ያስፈልጋል፡፡በተለይም በትርፈ ሰዓታችሁ ልትሰሩ የምትወዱትን ምንም አይነት የገንዝብ ግፊት ሳይኖርባችሁ ልትሰሩ የምትችሉት ስራን በመለየት መክሊታችሁን ወይንም ተስጦአችሁን ማወቅ ትችላላችሁ፡፡
4.  እውቀታችሁን ጨምሩ
ብዙ የተማሩ ብዙ ውጤታማ ሲሆኑ ይታያል፡፡ከአንድ ቦታ ስራ ለቃችሁ ለመሄድና ወደ ሌላ ስራ ለመቀየር ስታስቡ የምትቀይሩት ስራ ምን ያክል ህይወታችሁን እውቀታችሁን እንደሚቀይር ከግንዛቤ ማስገባት ያስፈልጋል፡፡እውቀትን የማይጨምርላችሁ ቦታ ላይ መገኘት በራሱ ኪሳራ ነው፡፡
5.  ውሳኔያችሁ የደሞዝ እድገትን ብቻ መሰረት አያድርግ
የስራ ለወጥ ስትዳርጉ ገንዘብ አንዱ ወሳኝ ነገር መሆኑ እሙን ነው፡፡ነገር ግን ብቸኛው መሆን የለበትም፡፡ሁል ጊዜም የደምወዝ ጭማሬን ብቻ አይተው ስራ የቀየሩ ሰዎች ሲፀፀቱ እንመለከታለን፡፡ገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ ስራ ወይንም ሙያ ስንቀይር ግን መሰረታዊ ከሆኑ ምክንያቶች ጋር የሚሰተያይ አይደለም፡፡ገንዘብን ብላችሁ ተስጥአችሁን የማጣት ጉዳይም ሊመጣ ስለሚችልና ደስታችሁም ያለው የምትወዱትን ስራ ከመስራት ጋር ተያይዞ ስለሆነ ገንዘብን ብቻ መሰረት አድርጋችሁ ስራ ወይንም ሙያን አትቀይሩ፡፡
6.  ማስካከል ይቻላል
ምንም አይነት የተሳሰተ ውሳኔ ብንወስንና ስራ ቀይረን የምንፈልገው ሆና ባናገኘው መደናበር የለብንም፡፡የቀየርነው ስራ የነበረንን ልምድ አስተሳሰብ አመለካከት ሊነጥቀን አይችልም፡፡ስለዚህም ለማስተካከል  ብዙ እድል አለን፡፡በስህተታችን ምክንያት ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡ከ70 ዓመቱ በኋላ ቢሊየነር የሆነ ግለሰብም ታሪክ የሚያሳየን አበቃለት አለቀለት የሚባል የህይወት ዘመን እንደሌለ ነው፡፡እስትንፋሳችን እሰካለች ድረስ እናስተካክለዋለን፡፡ዋናው ቀጣ ውሳኔያችን ደስታን የሚፈጥር ሆኖ መገኘት ይኖርበታል የሚለው ነው፡፡



















Comments

Popular Posts