የደካማ የስራ ሃላፊዎች ባህሪ
የደካማ የስራ ሃላፊዎች ባህሪ
የሚናገሩትን ሆኖ አለመገኘት
ሰዎች የሚናገሩትን
የማያደርጉ ሰዎችን ለመለየት ጥቂት ጊዜ ብቻ ነው የሚወስድባቸው፡፡ራሳችሁን ማድረግ የማትችሉትን ወይም ልትሰሩ የማትችሉትን
ነገር መናገር ምንም አንክን ለአጭሪ ጊዜ ተፅዕኖ ቢፈጥርም ለረዥም ጊዜ ግን መልካ ሰምን የሚያጎድፍ ነው፡፡እንናተ ልታደርጉት
የማትችሉትን ነገር ሰዎች እነዲያደርጉ መገፋፋት ወይም በንግግር ለማሳመን መሞከር የኋላኋላ ላይ ውጤቱ አያምርም፡፡
አዛዥ መሆን
ሃላፊ ሂድ ይላል መሪ
ግን እንሂድ ይላል፡፡ሰራተኞችን መዛዝ ብቻ የስራውን ውጤታማነት የሚገድል ነው፡፡ስለዚህም መሪዎች ተሳትፎ ማድረግ ካልቻሉ
የስራው ውድቀት መጀመርያ ነው፡፡በተለይመ ግዙፍ ውሳኔዎች የሚጠቁ ስራዎች ላይ መወሰን የማይችሉ ሰራተኞች ስራውን እንዲሰሩ
ማዝዝና አለመሳተፍ ከልፋት በቀር የሚያመጣው ለውጥ የለም፡፡
የሚያውቁትን ለሌሎች አለማካፈል
ሰራተኞች
ከሃላፊዎቻቸው ምንም መማር ካልቻሉ በስራቸው ላይ ውጤታማ የመሆን እድላቸው ጠባብ ነው፡፡እስቲ ያስቡት ስለ እያዳንዱ ስራ
ሰራተኞች የእርስዎን አቅጣጫ መስጠት ሲፈልጉ አሰልቺ ነው፡፡ስለዚህ ሰራተኞችን ማበቃት ከመሪዎች ይጠበቃል፡፡አንዳንድ ስራዎችን በራሳቸው
መስራት የሚችሉበትን አቀም ማዳበር ያስፈልጋል፡፡ሰራተኞች የማያውቁትን ነገር ወደ እረስዎ ይዘው መጥተው ተወው በቃ እኔ
እሰራለሁ የሚሉ ከሆነ የሰራተኛዎን ሞራል ይገድላሉ፡፡በቀጣይነትም በራስ መተማመን እንዳይኖረው ያደርጋሉ፡፡
Comments
Post a Comment