የመሪነት ባህርያትን ማዳበር




የመሪነት ባህርያትን ማዳበር 
በፕሬፌሽናል ህይወትዎ ብዙ ሰዎችን የሚያስተዳድሩ ከሆነ ብዙ ጫና ይኖርቦታል፡፡የመሪነት ቦታ የስራችን ውጤት ሙሉ የሚያደርግልን ቢሆንም ከሰውነታችን፣ከአዕምሮአችንና ከስሜታችን ብዙ የሚቀንስብን ነገር አለ፡፡ትንሽም ይሁን ብዙ ሰራተኞች ስናስተዳደር የሚጠበቅባቸውን እየተወጡና ስራቸውን በደስታ እየሠሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ ቀላል አይደለም፡፡
የሰራተኞች መነቃቃት 70 ፐርሰንቱ የሚሰነው በመሪዎቻቸው/ሃላፊዎቻቸው እንቅስቃሴ ነው ይለናል ጋሉፕ ያጠናው ጥናት፡፡ምንም ሊያደርጉ የማይችሏቸው አንዳንድ ሁኔታዎች ቢኖሩም በተመሳሳይ ደግሞ ሊያዳብሯቸው የሚችሏቸውና መልካም በመሆን እንዲቆሙና በጎ ተፅእኖ አንዲፈጥሩ የሚያስችለትን ስትራቴጂና ሞዴል መከተል ይችላሉ፡፡


















ስለአመራር ሁኔታዎ ሰዎች በአግርሞት ያነሳሉ?..በሰዎች ስሞ የሚነሳው በመልካም ጎኑ ነው በመጥፎ ጎን?
መሪ መሆን ከፈለጉ፡-
1.  ከሚያሰሯቸው ሰራተኞች ጋር ጊዜ ይኑሮት
ከሰራተኞች ጋር ጊዜ የሌላቸው ሰዎች ብዙ ነገራቸው ወደ አምባገነንተ ይለወጣል፡፡ከሰራተኞች ጋር የመወያያ ጊዜ ከሌሎት ሰራተኞች የሚፈልጉትን እንዴት ሊረዱ ይችላሉ፡፡ ለሰራተኞች ጊዜ መስጠትና አብሮ መወያት የአብሮነት ስሜትን ይፈጥራል፣ያስከብራል፣የሰራተኞችን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየት ያስችላል፣ችግርን በጋራ መፍታት ያስችላል፡፡ይህ ማለት ግን በትንሹም በትልቁም ከሰራተኞች ጋር ጊዜ ማሳለፍ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ሰራተኞች በጥቃቅን ስራዎች ጭምር ሃለፊዎች ጣልቃ ሲገቡባቸው የራሳቸውን አቅም ማዳበርን በራስ መተማመን ሊያሳድጉ አይችሉም፡፡


 









2.  ሃላፊነት መውሰድ
እንደመሪ ለሚወስዱትን መናቸውም እርምጃዎችና እነዚህ እርምጃዎች ለሚያመጡት ነገር ተጠያቂነትን መውሰድ ይልመዱ፡፡በሌሎች ሰዎች አያሳቡ፡፡ሰራተኞች ለሰሩት ስህተት ሃለፊነት መውሰድን እንዲማሩና ስህተት ሰርተው ደግሞ እንዳይፍረከረኩ እርስዎ አርዓያ በመሆን ያሳዋቸው፡፡ምክያቱም ሰራተኞች ስህተት ሲሰሩ በከፍተኛ ደረጃ ይደናበራሉና ነው፡፡የማረጋጋት ስራ መስራት ከመሪዎች ይጠበቃል፡፡በዚህም ጊዜ ሰራተኞች በእርስዎ ላይ መተማመን ያድርባቸዋል፡፡
3.  ለተሻለ ነገር ራስዎን ያሳድጉ
ሰዎች የሚመለከቱት የሚያነቃቃቸው ለተሻለ ነገር የሚያነሳሳቸው አርዓያዎችን ይፈልጋሉ፡፡ይህ ተፈጥሮዓዊ ነው፡፡ለራስ መሻሻል ቁርጠኝትን ማሳየት ሰራተኞችም ራሳቸውን እንዲያሻሽሉ በጎ ግፊትን ይፈጥራል፡፡ሌሎችም ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ በጎ ተፅዕኖን ያሳድራል፡፡ይህም የሚያሰሯቸው ሰራተኞችን ተጨማሪ አቅም መጠቀም ያስችላል፡፡

Comments

Popular Posts