ታንዛኒያን በኢኮኖሚ ቅኝት
በምስራቅ አፍሪካ አፍሪካ ታላለቅ ሀይቆች ክልል
የምትገኝ በሰሜን ከኬኒያ፣ኡጋንዳ በምዕራብ ከሩዋንዳ፣ብሩንዲ እና ዲኮምትራቲክ ሪፐብክ ኦፍ ኮንጎ በደቡብ
ከዛምቢያማላዊና ሞዛምቢክ እንዲሁም በመስራቅ ከህንድ ውቅያኖስ ጋር ተዋሰናለች፡፡የአፍሪካ ትልቁ ተራራ ኪላማንጀሮም የሚገኘው
በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ ነው፡፡የተባበሩት መንግስታት ባወጣው መረጃ መሰረት የሀገሪቱ ህዝብ ቁጥር 60 ሚሊየን ይጠጋል፡፡የዛሬው
የመዋዕለ ንዋይ ኢኮኖሚ ቅኝት ወደ ምስራቅ እፍሪካዊቷ ሀገር ታንዛኒያ ይወስደናል፡፡
የታንዛኒያ የቀድሞዋ ዋና ከተማ ዳሬሰላም የነበረች ሲሆን አሁን ለመንግስቱ መቀመጫ ሆና እያገለገለች የምትኘው ዶዶማ
ናት፡፡የፕሬዝደንታዊ ህገመንግሰት ሪፐብሊክ የሆነችው ታንዛኒያ አውራ ፓርቲ በሆነው የቻማ ቻ ማፑንዲዚ ፓርቲ ትመራለች፡፡ከዛሬ
2000 ሺህ ዓመት በፊት ከደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል ፈልሰው ወደ ታንዛኒያ የገቡ የደቡብ ኩሺቲክ ህዝቦች መኖርያ የሆነችው
ታንዛኒያ የኩሺቲክ እና ናይሎቲክ ተናጋሪ ህዝቦች በብዛት ይኖሩባታል፡፡
በአንደኛው የአለም ጦርነት ወቅት የምስራቅ አፍሪካዊቷ
ጀርመን በሚል በጀርምን ቅኝ ግዛት ውስጥ ትተዳደር ከነበረበት ወደ እንግሊዝ ቅኝ ግዛት የተላለፈች ሲሆን በ1963 እንደ
አውሮፓውያን አቆጣጠር ሙሉ ለሙሉ ከቅኝ ግዛት ነፃ ወጥታለች፡፡የሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በጥቅጥቅ ደኖች የተሸፈነ ሲሆን የአፍሪካ
ሶስት ታላላቅ ሀይቆችም በግዛቲቱ ስር ይገኛሉ፡፡አመቱን ሙሉ ሳያቋርጥ የሚፈሰውና በአፍሪካ ሁለተኛ የሆነው የካላምቦ ፏፏቴ
የሚገኘውም በታንዛኒያ ነው፡፡በታንዛኒያ ከ100 በላይ ቋንቋዎች ይነገራሉ፡፡ይህም ሀገሪቱን በመስራቅ አፍሪካ በቃንቋ ሀብት
ተጠቃሽ ሀገር ያደርጋታል፡፡ምንም እንኳ የሀገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ ሲሂዋሊኛ ቢሆንም በይፋ የተጠቀሰ የስራ ቋንቋ ግን የላትም፡፡
ከ40 በመቶ በላይ ከድህነነት ጠለል በታች ይኖሩ የነበሩ
ዜጎቿን ከዚህ የድህነት አዙሪት ለማውጣት ግዙፍ የኢኮሚ እንቅስሴዎችንና መሻሻያዎችን
በማድረግ በመስራቅ አፍሪካ ሶስተኛውንና በአለም አቀፍ ደረጃ በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገራት ደግሞ 5 ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለችው
ታንዛኒያ በአንድ ወቅት በተረጂነታቸው በስፋት ከሚጠቀሱ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ የምትመደብ ነበረች፡፡
በጣም ዘቅተኛ
ከሆነ የኢኮኖሚ ደረጃ በሰፊ ማሻሻያዎችና መዋቅራዊ ለወጦች አጠቀላይ ሀገራዊ የሀብት መጠን 50 ቢሊየን ዶላር ማድረስ የቻለችው ታንዛንያ ከ1986 ጀምሮ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሻሻልና
ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ውጤት ለማስመዘግብ በተሰራ ሰፊ ስራ ኢኮኖሚውን በአማካይ ከ5-6 በመቶ እያደገ ለሁለት አስርት
አመታት አስችለውታል፡፡
በዚህ የኢኮኖሚ
ሽግግር ታንዛኒያ በመንግስት የተያዙ የንግድና አምራች ተቋማትን በስፋ ወደ ግሉ ዘርፍና ከመንግሽጽ ጋር በሽርክና ወደ ሚሰሩ
አካላት ያሸጋገረች ሲሆን የኢንዱሰትሪው ዘርፍንም በማነቃቃት የተሻለ ውጤት አስመዘግባለች፡፡በአንድ ወቅት ሀገሪቱ ኢኮኖሚ በውጭ
ለጋሾች ችሮታ የሚንቀሳቀስበት ታሪክ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ታንዛንያውያን በራስ ሰርቶ መለወጥን እያጣጣሙት ይገኛሉ፡፡
በከፍታኛ ደረጃ
በግብርና ላይ የተመሰረተው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሀገሪቱ ወደ ውጪ የምትለከውን 80 በመቶ እንዲሁም የሀገሪቱን ለስራ የደረሰ ዜጋ
ግመሽ ያክሉ ተሰማርቶ የሚሰራበት ነው፡፡በግብርናው ላይ ያለውን ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥገኝነትም ወደ ኢንዱስትሪው ለማሻጋገር
በሀገሪቱ የተለያዩ ተግባራት የተከናወነ ሲሆን እስከ 2013 ባለው ጊዜም የኢንዱስትሪ ዘርፉ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ 22 በመቶ
መሸፈን የሚችልበት አቅም ተፈጥሯል፡፡በወቅቱም የማዕድን ማውጣት ስራ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ 3.3 በመቶ የሚሸፍን የነበረ ሲሆን
ከማዕድን ሀብቷም ወደ ውጪ ከሚላኩ ምርቶች ወርቅ 89 በመቶው የሚሸፍን ነው፡፡ሀገሪቱ በሌሎች የተፈጥሮ ማዕድናት የታደለች
ሲሆን አልማዝ፣የድንጋይ ከሰል፣ፓዞላና፣ጨው፣ጂፕሰም፣መዳብ፣ነሓስ የመሰሳሉ ማዕድናት በሀገሪቱ በስፋት ይገኛሉ፡፡
የወርቅ ዘመናዊ
የመምረት ስራ በሀገሪቱ በ1894 በጀርምን ወረራ ወቅት የተጀመረ ሲሆን የሰንከንኬ የወርቅ ማዕድን ቦታም የመጀመርያው ማምረቻ
ነበር፡፡የኒኬል ማዕድን ሀብት ክምችት መጠን በሀገሪቱ 290 ሺህ ቶን የሚጠጋ ሲሆን በ 3 ቢሊየን ዶላር አቅም የሚለማው
የድንጋይ ከሰል ሌላው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መሰረት ነው፡፡
በሀገሪቱ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚተዳደረው የታንዛኒያ
የአሌክትሪክ አቅርቦት ድርጅት በታንዛኒያ ያለው የአሌክትሪክ ሀይል ከፍተኛ ደርሻውን የሚሸፍን
ሲሆን በ2013 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ብቻ 6 ቢሊየን ኪሎዋት ሀይል በሰዓት ማምረት የሚችል አቅምን ታንዛኒያ ገንብታለች፡፡49
በመቶ የሚሆነው የሀገሪቱ የሀይል አቅርቦት ከተፈጥሮ ጋዝ የሚገኝ ሲሆን 28.9 በመቶ ከውሃ ሀይል እንዲሁም 20.4 ከተርማል የሚገኝ
ነው፡፡ሀገሪቱ በ2025 የሀይል ማመንጨት አቅሟን 10 ሺህ ሜጋዋት ለማድረስም እየሠራች ትገኛለች፡፡
በ2010 30 ትሪሊየን ኪውቢክ ጫማ የተፈጥሮ ጋዝ ክምች
እንዳለት በጥናት የተረጋገጥው ታንዛኒያ የተፈጥሮ ነዳጅ ሀብትም ባለቤት ነች፡፡
የውልድት መጠን በታንዛኒያ ከሳሃራ በታች ካሉ ሀገራት እጅግ ዝቅተኛ ሚባል ነው፡፡ከሀገሪቱ ህዝብ
2/5 የሚሆነውም ህዝብ ከ15 ዓመት በታች ሲሆን የዜጎች በህይወት የመኖርያ ጣርያም ከ50 ዓመት በላይ በአማካይ ይደርሳል፡፡የህፃነት
ሞትን ሀገሪቱ መቀነስ ችላለች፡፡በሀገሪቱ የዋጋ ንረት መጠን ከ5 በመቶ ያለዘለለ ሲሆን ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት እጅግ
ዝቅተኛው ነው፡፡ለስራ ከደረሰው የሀገሪቱ የሃይል ቁጥር ውስጥ አብዛኛው የስራ እድል የተፈጠረለት ሲሆን በ2006
ከነበረበት የ11.7 በመቶ የስራ ዐጥነት ደረጃ ወደ 10 በመቶ በ2016 ዝቅ ብሏል፡፡
በ2016
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ብቻ የሀገሪቱ የጋይናንስና የኢንሹራንስ አግልግሎት የ13.4 በመቶ እድገት ሲያስመዘግብ፣የኢንፎረሜሽንና
ኩሙኒኬሽ ዘርፉ የ13.5 በመቶ፣የግረናው ዘርፍ 2.7 በመቶ፣የማዕድን ልማት ዘርፍ 6.5 በመቶ እንዲሁም የሪል ስቴት ክፍሉ የ2.6
በመቶ እድገትን አስመዘግቧል፡፡በ2016 ሁለተኛው ሩብ ዓመት ከተመዘገብው ዝቅተኛ እድገት ውጪ ከ2010 እስከ 2017 ባሉት አመታት
ኢኮኖሚው በ7 በመቶ እድገትን ያሳየ ሲሆን አለም በፋይናንስ ቀውስ በምትታመሰበት የ2008 የአውሮፓውያን የፋይናንስ ቀውስ በመንግስት
ጠንካራ ቁጥጥር የሚደረግበት የታንዛኒያ የፋይናንስ ዘርፍ ከዚህ ቀውስ መዳን ችሏል፡፡የማይክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አስተዳደር ስርዓቷን
አጠናክራ መቀጠል ከቻለችም ኢኮኖሚው በተጠናከረ ሁኔታ እድገቱን አንደሚያስቀጥል የስነ ምጣኔ ምሁራን አምነት ነው፡፡
ሀገሪቱ
በተለይም በመሰረተ ልማት ዘርጋታና በሀይል ማምንጨት ላይ የምታውለው መዋዕለ ንዋይ የአማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን እድገት በይበልጥ በማሳደግ
አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚጠበቀውን ውጤት ማስገኘት አንደሚችል የአለም ባንክ ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡ሀገሪቱ የግል ዘርፍን ለማበረታት
የወሰደቻቸው የፖሊሰ ማሻሻያዎችም የግሉ ዘርፍን እድገት በማፋጠን የዜግች የስራ አድል በመፍጠር ሀገሪቱን እስከ 2030 ባለው ዓመት
ውስጥ ወደ መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ አቅም የሚፈጥር ነው፡፡
አጠቃላይ የታንዛኒያ የኢኮኖሚ እድገቷ አሁንም ግስጋሴንን እያሰየ ነው 45 በመቶ ከድህነት ወለል
በታች ይኖር የነበረውን ህዝብ በአሳማኝ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል፡፡በወጭ ምንዛሬ ገቢ የቱሪዝም ዘርፉ መሪ ሲሆን የግብርናው ዘርፍም
በተከታይነት ይቀጥላል፡፡የሀገሪቱ አጠቃላይ የምርት መጠን በ2010 ከነበረበት 31.4 ቢሊየን በ2017 ወደ 50.5 ቢሊየን ደርሷል፡፡የታንዛኒውያን አመታዊ አማካይ ግለሰብ ገቢ ከ1000 ዶላር
በላይ የደረሰ ሲሆን ከ10 ዓመት ከነበረበት የ620 ዶላር 380 ዶላር እድገት የታየበት ነው፡፡ታንዛኒያ ነፃነቷን ከቅኝ ግዛት
ካወጀች ከ1960ዎቹ ጅምሮ ባላት ሰላምና መረጋጋት ኢኮኖሚውም በተጨባጭ ሁኔታ እድገት መሳየት ችሏል የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨትመንቱም
ትርጉም ባለው መልኩ አድጓል፡፡፡፡ከ2017 እስከ 2026 ባለው ጊዜም የታንዛኒያ ኢኮኖሚ በአማካይ በ6 መቶ እንደሚያድግም ይጠበቃል፡፡
Comments
Post a Comment