ከፅዳት ሰራተኛነት እስከ ሚሊየነርነት


ከፅዳት ሰራተኛነት እስከ ሚሊየነርነት
ሺያን ኮንለን ተወልዶ ያደገው በአየርላንድ በምተገኝ ሮተንጋን በምትባል ትንሽ ከተማ ነው፡፡የቤተሰቡ ቁጠር 7 ነው፡፡እናትና አባቱን ጨምሮ ፡፡1000 ሄክታር መሬት ነበራቸው፡፡ቤተሰቦቹ ይህን ያህል ሄክታር መሬት ሀብት ይኑራቸው እንጂ ህይወታቸው እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡በአንድ ወቅትም ቤታቸው በባንክ እዳ ሊሸጥ የነበረበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር


















በልጅነቱ ያጋጠመው ይህ ሁኔታ ኮንለን ቤት ሊኖረው እንደሚገባና ቤት ያለው ሰው ኢኮኖሚያዊ አቋሙ የተደላደለ እንደሚሆን እንዲያስብ በዚህም ውስጥ እጣ ፈንታው የሪል ስቴት ስራ እንደሆነ ያመላከተው አጋጣሚ የተፈጠረው፡፡ በ1990 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የቆጠባትን 500 ዶላር ይዞ ወደ አሜሪካ ችካጎ አመራ፡፡የፅዳት ሰራተኛ ሆኖም ተቀጠረ፡፡’’ተራ ሰው ነበርኩ በጣም የሚገርሙ ስራዎችን እሰራ ነበር፡፡ ያለሁት አሜሪካ ነው፡፡የስራ ትንሽና ትልቅ የለውም እዚህ ፈለኩትን ብሰራ ማንም ግድ የለውም፡፡’’
በቀን የፅዳት ስራውን እየሰራ በማታ ደግሞ ቤቶችን ቀለም የመቀባት  ስራ እየሰራ ከቆየ ከጥቂት አመታት በኋላ ቤት ለመግዛት የሚያስችለውን ገንዘብ መቆጠብ ቻለ፡፡በዚህ ሂደት ውስጥ ሪል ስቴት ለሀብት ውጤታማ መንገድ መሆኑን ተረዳሁ የሚለው ኮንለን ከ1990 እስከ 2017 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ብዙ የህይወት  ውጣ ውረዶችን አሳልፏል፡፡የመልካም ጥረት ውጤቱ ሁሌም ስኬት ነውና ኋላ ላይም ስኬትን ሊቆናጠጣት እንደለማት አለቀረም አግኝቷታል፡፡
ኮንለን በሪል ስቴት ስራውን ሰጀምር አንድ ቤት የሚሸጥበት ዋጋ ከ20 ሺህ እስከ 30 ሺህ ይደርሳል ይህም ወደ ስኬት የገፋው ነበር፡፡’’አፓርትምንት በ230 ሺህ ዶላር አሻሽጬ ያገኘሁት የ400ሺህ ዶላር ኮሚሽን በህይወት ዘመኔ ያገኘሁት ትልቁ ገንዝብ ነበር በወቅቱ፡፡’’በዚያ ጊዜም ኮንለን በአመት የሚያገኘው 14 ሺህ ዶላር ይጠጋ ነበር፡፡ኮንለን የሪል ስቴት ቤቶችን ያሻሽጥ የነበረው በምሽት ሲሆን በሶስት አመታት ውስጥ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ዋነኛ ስኬታማ ደላሎች አንዱ መሆን ችሏል፡፡የፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ቀን ቀን ይሰራል ማታ ማታ የቤት ሽያጭች ድለላውን ያካሂዳል፡፡ጠንክሮ ሰራ ተለወጠ፡፡ለስኬቱም ደከመኝ ይህ ስራ ሰለቸኝ ሳይል መስራቱ የሚጠቅሰው ነው፡፡
ተተርጉሞ የተጫነው በጥሩሰው ገረሱ

Comments

Popular Posts