የስኬታማ ግለሰቦች ልምድ
የስኬታማ ግለሰቦች ልምድ
ሀብት ማካበት
የብዙ አመታትን ብልሃት የተሞላበት ውሳኔ ይጠይቃል፡፡በሙያም ይሁን በገንዘብ በኩል ማለት ነው፡፡በመቶ የሚቆጠሩ ሚሊየነሮችን
ያነጋገረ አንድ ግለሰብ ሀብታም ለመሆን ከዚህም ባሻገር አንዳንድ የህይወት ልምዶች ሊኖሩን ይገባል ይለናል፡፡
አካውንታንትና
የፋይናንስ ፕላነር የሆነው ቶም ኮርሊ 233 ሚሊየነሮችን በህይወት ልምዳቸው ዙርያ አነጋግሯል ፡፡እንዲሁም የቀን ተቀን
ተግባሮቻቸውን ጭምር አጥንቷል፡፡አብዛኛዎቹ በራሳቸው ጥረት ሀብት ያፈሩ ናቸው፡፡ይህንንም ምላሽ ይዞ በአመት ከ35 ዶላር በታች
ከሚያገኙ ግለሰቦች ምላሽም ጋር አነፃፅሯል፡፡
ከፍተኛ ሽያጭ
በነበረው ቼንጅ ዩር ሀቢት ቼንጅ ዩር ላይፍ በተሰኘው መፅሃፉ
ኮርሌይ እንደሚገልፀው ሀብታም ግለሰቦች ለስኬታች በአንድም በሌላ መልኩ ራሳቸውን በአንድ ምንገድ ገርተዋል፡፡ራሳቸው የህይወት
ልምድን አዳብረዋል፡፡ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡት የህይወት ልመዶች ብዙዎቹ የሚጋሩት ነው፡፡
1. በጥዋት መነሳት
50 በመቶ የሚሆኑትና በራሳቸው ጥረት ሚሊየነር የሆኑት ባለሀብቶች የስራ ሰዓታቸው ከመጀመሩ ከ3 ሰዓት በፊት
ከእንቅልፋቸው ይነቃሉ፡፡ይህንንም ሰዓት የራሳቸውን ፕሮጀክት ለመንደፍ፣የቀን የስራ ውሎአቸውን ዕቅድ ለማውጣት እና የአካል
ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ይጠቀሙበታል፡፡እነዚህን ዋነኛ ሶስት ነገሮች ለማከናወን ከሌሊቱ አስራ እንደ ሰዓት ሁሌም መነሳት
ሕይወትን ለመቆጣጠር ያስችላል፡፡የራሳችሁን ህይወት እየተቆጣጠራችሁ እንዲሰማችሁ ያደርጋል በራስ መተማመናችሁንም ይጨምራል፡፡
2. ብዙ ማንበብ
88 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ መላሽ ባለሀብቶች 30 ደቂቃ
ወይም ከዚያ በላይ በቀን በማንበብ ራሳቸውን ለማሻሻል ያውላሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ለመዝናናት አያነቡም የስኬታማ ግለሰቦች
ግለታሪክ፣ታሪኮች እና ራስን መርዳት የሚያስችሉ መፃሃፍትን ማንበብ ያዘወትራሉ፡፡ መልካም የሆነ ልብወልድን ማንበብም ይረዳል፡፡የሳይንስ
ጥናት እንደሚያሳየውም ለመደሰት ማንበብ የስራ ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል፡፡ከትንሽ ተነስተው ትልቅ ደረጃ የደረሱ ስኬታማ
ግለሰቦችንም ታሪክ ማንበብ ያንፃል፡፡ ዝነኛው ኢንቬስተርና በራሱ ጥረት ቢሊየነር መሆን የቻለው ዋረን ቡፌት እንደሚናገረው
ማንበብ ትልቁ የህይወት ልምዱ ነው፡፡
3. ከ15-30
ደቂቃ የፅሞና ጊዜ
አብዛኛዎቹ ሚሊየነሮች በህይወታቸው እየተከናወነ ስላለው
ጉዳይ ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ገዜ ሰጥተው ያሰላስላሉ፡፡ሀብታሞቹ ብቻቸውን ሆነው ለማሰላሰል ጥዋትን ይመርጣሉ፡፡ቢያንስ ለ15
ደቂቃ በቀን፡፡ይህም በስራቸው፣በጤናቸው ከሰዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት
ላይ ውጤቱ ይታያል፡፡ከራስ ጋር የፅሞና ሰዓት እነዲኖር ማድረግ ጭነቀትንም ይቀንሳል፡፡በስራ ቦታ ለሁለት ደቂቃ
በአተነፋፈሶ ላይ ብቻ ትኩረትዎን አድርገው ቢቆዩ ዘና እንዲሉ ያደርጎታል፡፡
4. የአካል
ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
አዕምሮን ለማንፃትና ለማነቃቃት ይረዳል፡፡ እንደ ኮርሌይ ገለፃ በጥናቱ ውስጥ ከተካተቱት 76 በመቶ የሚሆኑት 30 ደቂቃ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፡፡ሳይክል መንዳት መራመድን የመሳሰሉትን በየቀኑ ይሰራሉ፡፡ብዙዎቹ ውጤታማ የቢዝነስ መሪዎች
ሩጫን ያዘወትራሉ፡፡ቢሊየነሩ ሪቻርድ ብራንሰን ለምሳሌ የጥዋት ልምዱ አስራ አንድ ሰዓት ለሊት ይነሳል ቴኒስ ይጫወታል ወይም
ብስክሌት ያሽከረክራል፡፡ ይህም ውጤታማነቱን በሁለት እጥፍ ጨምሮለታል፡፡
5. አርአያ
ከሆኑን ግለሰቦች ጋር ቆይታ ማድረግ
ራስህን ከምታስተያየቸው ወይም እነሱን ብሆን ብለህ
ከምታስባቸው ጋር ስኬትህ ይገናኛል ይላል ኮርሌይ፡፡በሕይወት መንገድህ ውስጥ ስኬታማ ግለሰቦች ከሌሉ ችግር የለውም የሌሎችን
ልምድ በብዙ መንገድ ማግኘት ትችላለህ፡፡ራሳቸውን ለዚህ የሰጡ ጊዜያቸውንና ለሌሎች ሰዎች ተሞክሮአቸውን ለማካፈል የተዘጋጁ
ብዙዎች አሉ፡፡ወይም ደግሞ እንዲህ አይነት የራሳቸውን ተሞክሮ ማካፈል ፍላጎት ካላቸው ቡድኖች ጋር ግንኙነት መፍጠር
ይቻላል፡፡ከዚያም ወዳጅነትን ማጠንከር፡፡ውጤታማ የሆኑ ሰዎች መጥፎ አስተሳሰብና ጠማማነት ካለቸው ግለሰቦች ራሳቸውን ያራቁ
ናቸው፡፡
6. የራስን
ግብ ማስቀመጥ
አብዛኛዎቹ በራሳቸው ጥረት ሚሊየነር የሆኑ ሰዎች ሀብታም
ለመሆን ያቅዳሉ ያሳኩታልም፡፡ 80 በመቶ የሚሆኑት ሀብታሞች ግባቸውን ለማሳካት በከፍተኛ ሁኔታ ይሰራሉ፡፡የቀን እቅዳቸውንም
ሆነ የረዥም ጊዜ ግባቸውን ያዛምዳሉ፡፡መሰላልህን በሌሎች ሰዎች ግድግዳ ላይ አስደግፈህ ምርጥ የሆኑ ግዜዎችህን መሰላሉን
ለመውጣት አታባክን፡፡የራስህን ግድግዳ ፈልግ፡፡ የራስህን ህልም የራስህን ግብ አስቀምጥ፡፡ይህን ለማሳከት ስራ፡፡
7. በቂ
የሆነ እንቅልፍ ማግኘት
አልበርት አንስታይን በቀን 10 ሰዓት ያክል የምሽት
እንቅልፍ ይተኛል፡፡በደንብ ስታርፍ በደንብ መስራት ትችላለህ፡፡ከ89 በመቶ በላይ ሚሊየነሮች በቀን ከ7 እስከ 8 ሰዓት
እንቅልፍ ይተኛሉ፡፡በቂ እንቅልፍ ማግኘት ለስኬት ወሳኝ ነው፡፡ከፈጠራ ችሎታና የማሰላሰል አቅም ጋር በእጅጉ የተያያዘ ስለሆነ ለስኬት
በቂ እንቅልፍ ማግኘት አስፈላጊ ነው፡፡
8. የገቢ
አድማስን ማስፋት
በራሳቸው ቢሊየነር የሆኑ ግለሰቦች በአንድ የገቢ ምንጭ ላይ
አይንጠለጠሉም፡፡ብዙ የገቢ ምንጭን ያዳብራሉ፡፡ስለዚህ ምን ያክል የገቢ ምንጮች ይኖራቸው ይሆን?ከ65 በመቶ በላይ የሚሆኑት
ስኬታማ ሚሊየነሮች ከሶስት በላይ ገቢ ምንጭ አላቸው፡፡ሪል ስቴት እና አክሲዮን የሚጠቀሱት ዋነኞቹ ናቸው፡፡የገቢ ምንጭን
ማስፋት ሁሌም አይቀሬ የሆነውን የኢኮኖሚ ቀውስን ለመቋቋምም ይረዳል፡፡
9. ሰዓታችንን
የሚያባክኑ ግሰለቦችን መራቅ
ገንዘብ ብቸኛው የሀብት ምንጭ አይደለም፡፡ጊዜ ወሳኝ ነው፡፡በማይረባ
ነገር ጊዜያችንን ካባከን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ያንን ሰዓት ተሰናበትነው ማለት ነው፡፡አንዴ ካመለጠ ጊዜ
አይመለስም፡፡በየትኞቹ የስልክ ሆነ ኢነተርኔት አፕሊኬሽች ላይ ገዜያችሁን እንደምታጠፉ ምረጡ፡፡በኢንተርኔት ላይ ሰትቀመጡ ብዙ
ጊዜያችሁን እናንተን ሊያንፁ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜያችሁን ኢንስታግራም አልያም ደግሞ ኔትፊክስ ላይ
በማዋል ውድ ጊዜያችሁን አትክሰሩ፡፡ጊዜ ከሁሉም ሪስክ በላይ መሆኑን ስትረዱ ጊዜያችሁን እንዴት ማዋል እንዳለባችሁ
ይገባችኋል፡፡
በጥሩሰው ገረሱ ተተርጉሞ ተጫነ
Comments
Post a Comment