እንደ ሶኬት ከህይወታችሁ ልትነቅሏቸው የሚገቡ አይነት ሰዎች
እንደ ሶኬት ከህይወታችሁ ልትነቅሏቸው የሚገቡ አይነት ሰዎች
መርዛማ ሰዎች የአመክንዮን ነገር ገደል የሚከቱ
ናቸው፡፡አንዳንዶቹ በሌሎች ሰዎች ላይ ስለሚያስከትሉት ቀውስ አያውቁም፡፡አንዳንዶቹ ደግሞ ብጥብጥ በመፍጠርና የሌሎች ሰዎች
ጉዳይ ውስጥ በመግባት በሚፈጠረው ቀውስ የሚደሰቱ ናቸው፡፡
መርዛማ ሰዎች ገዜያችሁም ሆነ ጉልበታችሁ አይገባቸውም፡፡ነገር
ግን ብዙውን ግዜያችሁንና ጉልበታችሁን ይሻማሉ፡፡መርዛማ ሰዎች አላስፈላጊ ውስብሰቦችን ይፈጥራሉ፡፡በተለይ ደግሞ ጭንቀትን፡፡
ሰዎች ሊገነቧችሁ ይችላሉ አልያ ደግሞ ሊያፈርሷችሁ ይችላሉ፡፡
በቅርቡ የጀርመን የፍሬደሪክ ሺለር ዩነቨርሲቲ ያወጣው ጥናት
እነደሚያመለክተው መርዛም ሰዎች አደገኞች ናቸው፡፡ከእነዚህ ሰዎች ጋር ማሳለፍ በአዕምሮ ላይ እጅግ ከፍተኛ የውጥረት ጫናን
ይፈጥራል፡፡አነዚህ ሰዎች አዕምሮን በአላስፈላጊ ጭንቀት ውስጥ ከመክተታቸውም በላይ በጊዜ ዞር ካለተደረጉ የህይወትን ስኬትም
የሚያጨናግፉ ናቸው፡፡
ሀሜተኞች
ታልቅ ሰዎች ሀሳብን ያወራሉ መካከለኛ የሆኑት ስለሁኔታዎች
ያወራሉ በጣም ትናንሽ ጭንቅላቶች ስለሰው ያወራሉ፡፡ኤሊኖር
ሩዝቬልት
ሀሜተኞች ደስታቸውን የሚያገኙት በሌሎች አለመሳካት ነው/ሌሎች
ሳይሳካላቸው ሲቀር ነው/፡፡ስለዚህ እነዚህን ሰዎች በመራቅ ስለሰዎች ጥሩ መልካም ከሚያወሩ ጋር ወዳጅነትን መፍጠር ጤናማ
ያደርጋል
ስሜታዊ/ምሬታዊ
ሰዎች
በምንም አይነት ስሜታቸውን መቆጣጠር የማይችሉ መጥፎ ስሜታቸውን
በተደጋጋሚ የሚያጋቡ አይነቶች ናቸው፡፡እነዚህ አይነት ሰዎች በተደጋጋሚ ምሬት የሚያወሩ ስለሆኑ ይህን ወደ ህይወታችሁ ያጋቡባችኀዋል፡፡ምሬታችው
ማቆሚያ የለውም፡፡
ቅናተኛ ሰዎች
እንደዚህ አይነት
ሰዎች መልካም ቢሆንላቸው እንኳን የሚደሰቱ አይነቶች አይደሉም፡፡ሌሎች ስለተደረገላቸው ነገር የሚጨነቁ ናቸው፡፡ሁለግዜም በአንድ
ነገር ከእኛ የሚሻል ሰው አለ፡፡እነዚህ ሰዎች ግን ይህን አምነው የሚቀበሉ አይደሉም በሁሉም ነገር ይቀናሉ፡፡ሰዎች ስለተደረገላቸው
ነገር በክፉ ቅናት ውስጥ ይዋኛሉ፡፡እንደዚህ አይነት ሰዎች በህይወታችን ስላለን ነገር ደስተኛ እናድንሆን የሚያደርግን ስሜት
የሚያጋቡ ናቸው፡፡
በዝባዦች Manipulator
የምትወዱትን
የምትጠሉትን የሚያስደስታችሁን የሚያስከፋችሁን ነገር ሁሉ ያውቃሉ፡፡ይህን ለግላዊ ጥቅማቸው ያውላሉ፡፡እንደዚህ አይነት ሰዎች ከእናንተ
አንድ የሚፈልጉት ድብቅ አጀንዳ አላቸው፡፡ወደ ኋላ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ያላችሁን ግንኙነት ብትቃኙት የወሰዱባችሁ ነገር ብዙ
ነው፡፡
ጨለምተኞች
እነዚህ በገቡበት ቦታ
ሁሉን ነገር የሚያጨልሙ ሙቀት እንኳን ቢሆን ቦታውን በረዶ የሚያደርጉ ናቸው፡፡አዕሮአችሁን ተቆጣጠረውት ባዶ ሰውነታችሁን
ያስቀሩታል፡፡ክፉ ነገር ብቻ እንዲታያችሁ ተስፋ የሚባል ነገር እንደሌለ ይነግሯችኋል፡፡በብርሃን ተከባችሁ ጨለማ
ይውጣችኋል፡፡በቶሎ መላቀቅ ያስፈልጋችኋል፡፡አለም ብዙ መልካም ብዙ መጥፎ ነገሮች አሏት፡፡ሁሉንም ጎን ማየት ይገባል፡፡
ፈራጅ The Judgmental
ምንም ብትነግሯቸው
ትክክል እንዳልሆናችሁ ይነግሯችኋል፡፡በጣም የምተወዷቸውን ነገሮች ሁሉ በፍርጃቸው ያጠፉባችኋል፡፡የተለየ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች
ከመማር ይልቅ ሁሉንም ነገር መቃወም ባህሪያቸው ነው፡፡
ግብዞች
ምንም ነገር አድርጉ ከእነሱ ጋር እየተፎካከራችሁ እነደሆነ ይሰማቸዋል፡፡በስራ
ቦታቸውም ሆነ በህይወታቸው ያለመተማመን ስሜት ስለሚሰማቸው ሁሌም ይጋጯችኋል፡፡
አይታወቄዎች
ትክክለኛ
ባህሪያቸው ምን እነደሆነ አይታወቅም፡፡የሚጨበጡም አይደሉም፡፡ዘሬ መልካም ነገ ክፉ ዛሬ ፈገግታ ነገ ግልምጫ ብቻ በየትኛው
ሰዓት ምን እንደሚሆኑ አይታወቅም፡፡ህይወታችሁን አንደ ባህሪያቸው ያመሳቅሉታል፡፡እነዚህን መለየትና መፍትሄ መፈለግ ከባድ
ነው፡፡ዛሬ ትኩስ ነገ በራድ ዛሬ ብጫ ነገ ቀይ አረንጓዴ ዥንጉርጉር ይሆናሉ፡፡ከፉ ሲባሉ ደግ ደግ ሲባሉ ክፉ ቀረቡ ሲባሉ
የሚርቁ ብቻ ሁሉም ነገራቸው ተለዋዋጭ ነው፡፡
Comments
Post a Comment