የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት
ኢትዮጵያ
ለዓመታት
በኬንያ
የበላይነት
ተይዞ
የቆየውን
የምሥራቅ
አፍሪካ
የኢኮኖሚ
የበላይነት
ለመውሰድ
ተቃርባለች፡፡ከስምንት
ዓመታት
በፊት
የሁለቱ
አገሮች
ኢኮኖሚ
ዓመታዊ
ዕድገት
ከጠቅላላ
የአገር
ውስጥ
ምርት
አኳያ
ሲነፃፀር
ኬንያ
ኢትዮጵያን
በከፍተኛ ቁጥር
ትበልጥ
ነበር፡፡
እ.ኤ.አ.
በ2000
የኬንያ
ኢኮኖሚ
የ14
ቢሊዮን
ዶላር
ዓመታዊ
የጠቅላላ
ምርት
ዕድገት
እንደነበረው
ይገመት
ነበር፡፡
በአንፃሩ
የኢትዮጵያ
ኢኮኖሚ
በግማሽ
ያህል
ቀንሶ
ማለትም
በስምንት
ቢሊዮን
ዶላር
ገደማ
ይከተል
እንደነበር
መረጃዎች
ይጠቁማሉ፡፡
ንዲህ የነበረው የሁለቱ አገሮች የኢኮኖሚ ዕድገት ልዩነት በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ እየጠበበ መጥቶ፣ኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት ኬንያን መብለጥ እንደምትጀምር የሚያሳዩ መረጃዎች ይፋ ወጥተዋል፡፡ የአፍሪካ ልማት ባንክን ጨምሮ ሌሎች አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የሚሳተፉበት፣ ዓመታዊው የአፍሪካ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴና ዕድገትን የሚቃኘው ሪፖርትን መሠረት ያደረጉ ትንበያዎች እንደሚያረጋግጡት፣ ዘንድሮ ኢትዮጵያ የሚኖራት የኢኮኖሚ ደረጃ በምሥራቅ አፍሪካ የበላይ እንድትሆን የሚያበቃት ነው፡፡ ለዚህም በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እየተመዘገቡ ያሉ
ውጤቶችና የሀገሪቱ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትምንት እድገት በምክንያትንት ከሚጠቀሱት መካከል ወነኞቹ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች፡፣ ለዚህም በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የተያያዘችው ርብርብ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርክ ልማቷ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ለኢንዱስትሪ ልማቱ ከፍተኛ ፋይዳ ላለው ለውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በሰጠችው ትኩረትም የኢንቨስትመንቱ ፍሰት ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ መጥቷል፡፡ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለቴክኖሎጂና እውቀት ሽግግር እንዲሁም ለሥራ ዕድል ፈጠራ ዓይነተኛ ሚና ያለው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በሁሉም ሀገር የሚፈለግ እንደመሆኑ ሁሌም ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት እንደሚገባ የዘርፉ ባለሙያዎች ያስገነዝባሉ፡፡በኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እየጨመረ ይገኛል፡፡ ከ8እና 9 ዓመት በፊት በዓመት ከ1
ቢሊዮን ዶላር የማይበልጠው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ባለፈው ዓመት ብቻ 3 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ከኢንቨስትምንት ኮሚሽን የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከዚህ የበለጠ ደረጃ ላይ ሊደረስ እንደሚችል በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አመላካች ናቸው፡፡ በተለይም መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱና
የሚሰጡ ማበረታቻዎች እንዲሁም በኢንቨሰትምንት ዘርፉ ለመሰማራት ጥያቄ እያቀረቡ የሚገኙ ግዙፍ የአለማችን ድርጅቶች ለዚህ አንደማሳያ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
መንግሥት ትኩረቱን በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ላይ ማድረጉ ለኢንቭሰትምንቱ ዘርፍ መስፋፋት
እንደ መልካም አጋጣሚ የሚጠቀስ ነው። በአለማችን ላይ ላይ ያሉ
ተሞክሮዎች የሚያሳዩት ለእድገት የማኑፋክቸሪንግ ኢነዱሰትሪው መስፋፋት ወሳኝ መሆኑን ነው፡፡በተለይም ለቆዳ፣ ለጫማና አልባሳት ልዩ ትኩረትን የሰጡት እንደ ቻይና፣ ባንግላዴሽ ቬትናምና የደቡብ ምሥራቅ ሀገሮች ከፍተኛ እድገት የማመዝገባቸው ሚስጢር ይኸው ለማኑፋከቸሪንግ
ዘርፍ የሰጡት ትኩረት ነው። ይህ ሁኔታ የሚያሳየው ደግሞ ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እየሰራችበት ያለ ዘርፍ በመሆኑ እንደነሱ ውጤታማ የመሆን ሁኔታው ከእርግጠኛነት በላይ መሆኑን ነው እንደዘርፉ ተንታኞች ገለፃ፡፡
ቻይና በዓለም ሁለተኛዋ በኢኮኖሚ ያደገች አገር እንደመሆኗ የሕዝቧም የሀብት መጠን በዚያው ልክ አሻቀቧል፤ የሠራተኛ ደመወዝም እየጨመረ ነው፤ በዚህ ምክንያት ኢንቨሰትመንቷን ወደ ሌላ አገር የማሻገር አካሄደን እየተከተለች ትገኛለች። በዚህ ረገድ ከአፍሪካ የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነት ሰፊውን ድርሻ የምትወስደው ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የዚህ እድል ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡
አገሪቱ ካላት ምቹ የኢንቨስትምንት ሁኔታ ባሻገር ለቆዳና ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም ለሌሎች
የኢንቨስትመንት ስራዎች የሚሆን ሰፊ የሰው ጉልበት ያለባት አገር መሆኗ በራሱ ተወዳዳሪ ያደርጋታል፤ ይህንን የሰው ኃይል ወደ ሥራ ለማስገባት ለሚፈልጉ ባለሀብቶችም ምቹ ናት። በዚህ ምክንያት በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ የሚጨምር መሆኑ የብዙዎች እመነት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ዘርፉን ለማበረታታት ከምትከተለው አቅጣጫ በተጨማሪ በኃይል አቅርቦት ዙሪያ እያከናወነች ያለው ተግባር ለኢንቨስትምንት ሌላው በእጅጉ ተመራጭ የሚያደርጋት ጉዳይ ነው። ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ምንም እንኳን ከቀኝ ግዛት ከተላቀቁ 55
ዓመታትን ያስቆጠሩ ቢሆንም በተለይም ማኑፋክቸሪግ ዘርፋቸውን አንድ እርምጃ ማራመድ የቻለ አይደለም በመሆኑም አገሪቱ እነዚህን ዕድሎች ተጠቅማ ወደፊት መገስገስ የሚያስችላት ብቃት ላይ ትገኛለች።የስነ ምጣኔ ምሁራን እንደሚያስቀምጡት በኢትዮጵያ የተመዘገበውን ፈጣይና ተከታታይነት ያለው አኮኖሚ አጠናክሮ ለመስቀጠል የሚረዳት
የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትምንትን ለማሳደግ ሦስት መሠረታዊ ምቹ አጋጣሚዎች አሉ፤ አንደኛ የሰው ኃይል፣ ሁለተኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ፋብሪካዎችን መገንባት መቻሉና በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ በዓለም በጣም ርካሽ የሚባል የኤሌክትሪክ ኃይል ዋጋ ያለበት መሆኑ ነው፡፡ስለዚህ ከቻይናም ይሁን ከባንግላዴሽ አልያም ከምሥራቅ ኢዢያም እንዲሁም ከአውሮፓ ሀገሮች ወደ አፍሪካ አይናቸውን የሚያማትሩ ግዙፍ ድርጅቶች የጨርቃ ጨርቅ፣ የጫማ፣ የቆዳ ፋብሪካዎች ወይም ሌሎች ፋብሪካዎችን መገንባትን ሲያስቡ ተመራጭ የሚያደርጉት ኢትዮጵያን ነው፡፡
አገሪቱ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተሻለ ሁኔታ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የመሳብ ዕድል ያላት ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ካፒታልን በሚያመጣው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ ትኩረቷን ማድረጓ አሁን እያገኘች ያለውን ከ3
ቢሊዮን ዶላር ያልበለጠ ገቢ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር ከፍ እንደምታደርገው ማሳያም ጭምር ነው፡፡
በዓለም ላይ በተለይም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ውድድር አለ፡፡ ጎረቤት ሀገሮችም ኢትዮጵያ እንደምታደርገው ሁሉ የወጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ራሳቸውን በከፍተኛ ሁኔታ እያስተዋወቁ ናቸው። ይህንን ግንዛቤ በመወስደም መንግስት ለውጪ
ቀጥተኛ ኢንቨስትምንተ ምቹ የሆኑ የኢንዱሰትሪ ፓርኮችን በስፋት እየገነባ ይገኛል፡፡በእነዚህ የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ግዙፍ የሆኑና
ታወቂ የአለም አቀፍ አምራች ድርጅቶች ገብተው እየሰሩ ይገኛል፡፡ይህም ለውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትምንት ማደግ የበኩል ድርሻ የሚወጣ
ነው፡፡
በ2016 እንደ
አውሮፓውያን አቆጣር ወደ አፍሪካ የመጣው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 51 ቢሊዮን ዶላር የነበር ሲሆን ይህበዓለም ላይ ከነበረው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት አምስት በመቶውን ብቻ የሚወስድ ነው፡፡ በመሆኑም ወደ አፍሪካ ኢንቨስትመንቱን ለመሳብ ብዙ መስራት እንደሚኖርበት ማሳያ ነው፡፡ቻይና በአሜሪካን ብቻ 45
ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ያደረገች ሲሆን ከዓለም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትም 90 ቢሊዮን ዶላር አግኝታለች፡፡ ሕንድ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቭትምንተ መጠኗም 65
ቢሊዮን ደርሷል፡፡54 ሀገሮች ያሉባት አፍሪካ ላይ መድረስ የቻለችው 51 ቢሊዮን ዶላር፡፡
መንግስት ለውጪ
ቀጥተኛ ኢንቨስትምንት ያደረገውን ትኩረት ያክልም በመጪው ቀጣይ ጊዘያትም የሀገራችን ኢኮኖሚን በስፋት ያንቀሳቅሳሉ ተብለው
የሚገመቱ የሀገር ውስጥ ድርጅቶችን በማበረታታቱ ረገድም መንግስተ ሰፊ ትኩረት ሰጥቶ አየሰራ ይገኛል፡፡ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከገቡት መካከል የተወሰኑት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተወሰኑት ደግሞ ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በጋራ የሚሰሩ ናቸው፡፡ ይህም በእውቀት ሽግግሩ ረገድ የሚያበረክተው
አስተዋፅ ከፍተኛ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የውጪ
ቀጥታ ኢንቨስትምንት ከሁለት ዓመት በኋላ በዓመት አምስት ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገሮች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ሥራዎች 94 ሺ ሚጠጉ ሲሆን በከዚህ ውስጥ 15
በመቶውን ድርሻ የያዘው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነው፡፡ ይህም ኢንቨስትመንቱ ግዙፍ የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑን የሚያመላክት ነው፡፡ ከሌሎቹ ሀገራት የውጪ ኢንቨሰትምንት አንፃር የኢትዮጵያን ለየት የሚየደርገው ቬሌሎች ሀገራት የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨሰትምንት ካፒታል መሠረት ያደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን ለብዙሃን የስራ ዕደል መፍጠርን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ለዚህም እነደመሳያ የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ ወደ 60
ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡
ሀገሪቱ እያስመዘገበች ያለቸው ግዙፍ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትምንት በቀጣነትም እድገቱ እየቸመረ እነደሚመጣ ምሁራን
እየተነጋሩ ሲሆን በተለይም የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎችን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ የውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቱ አሁን ካለበት በቀጣ
አመታት በሁለት እጥፍ ሊያድግ እንደሚችልም ብዙሃን የሚስማሙበት ሀሳብ ነው፡፡ይህም ለብዙ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር ከማስቻሉም
ባሻገርም እየተመዘገበ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እድገት አጠናክሮ በማስቀጠሉ ረገድ የሚያበርከተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
Comments
Post a Comment