ስኬት






ስኬት


በስኬት ማማ ላይ ተቆናጠው ይበልጥ ውጤታማ እሆን ነበር ብለው ከሚቆጩ ግለሰቦች አንዱ፡፡የበርክሻየር ሀዝዌይ ባለቤትና መስራች የአለማችን ቁጥር ሁለት ሀብታም፡፡ዋረን ቡፌት፡፡ሁላችንም ብንሆን ቢበዛ በዚህች ምድር ላይ ያለን የቆይታ እድሜ ቢበዛ 80ሺህ ሰዓት ነው፡፡እኔ 35 ሺህ ያክሉን ተጠቅሜያለሁ ይለናል፡፡ዋረን ቡፌት፡፡
መጀመርያ በአንድ የአየር መንገድ ውስጥ አካውንታት ሆኖ ተቀጠረ የማይደሰትበት የህይወት ታሪክ ክፈሉ ነው፡፡ሁለተኛ ላይም በኢንቨስትመንት ባንክ ውስጥ የመቀጠር ዕድሉን አገኘ፡፡ ይኸኛው ደግሞ ይበልጥ አሰልቺው ነበር፡፡በመጨረሻም ለ14 ዓመታት በማይክሮሶፎት ድርጅት ውስጥ አገለገለ ትልቅ የህይወቱ ምርጥ ቦታ፡፡አሁን ደግሞ የራሱ ሀብት ባለቤት፡፡
በእነዚህ ሁሉ ዓመታት ስራ እንዴት ህይወትን በእጅጉ እንደሚነካ ተገንዝቢያለሁ ህይወትም ስራን እንዲሁ፡፡ወደ ኋላ የጎተተኝንም ሆነ ወደፊት ያስፈነጠረኝን ሁኔታ ተመልክቻለሁ፡፡ምን ማድረግም እንደለብኝ ተምሬያለሁ፡፡ምን መስራት እንደሌለብኝም ጭምር፡፡አሁን እጅግ ባለጠጋ ነኝ ነገር ግን ወደ ኋላ መለስ ብዬ የህይወት ጉዞዬን ሰመለከት ስራ ከመጀመሬ በፊት እነዚህን 10 ነገሮች ቀድሜ አውቄ ቢሆን ኖሮ እላለሁ፡፡
የመጀመርያው
1.  የመግባባት ችሎታ ነው
የመግባባት ችሎታ ከሌለህ ሴትን ልጅ በጭለማ እንደመጥቀስ ነው፡፡ብዙ ሰዎች ስማርት ናቸው፡፡የራስህን ቢዝነስ መጀመር ከፈለክ አንተም ያ እድሉ አለህ፡፡ስማርት መሆን ብቻ ግን በቂ አይደለም፡፡የመግባባት ራስን የመግለፅ ችሎታ ወሳኝ ነው፡፡ስማርት የሆኑ ሰዎች አቀራረባቸው የሚስብ ነው፡፡ራሳቸውን መግለፅ ይችላሉ፡፡ይህን በመፀፍና በመለማመድ ማዳበር ይቻላል፡፡በጣም ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን ለማስረዳት ተለማመድ፡፡መጥፎ አስተያየቶችን አትፍራ፡፡ልምድህን ማጎልበት ቀጥል፡፡

2.  በመጀመርያ ስራህ ፍፁምነት አትጨነቅ
የመጀመርያ የስራ ውጤትህ እንደምትፈልገው አይነት ላይሆን ይችላል፡፡ፍፁም የሆነ ነገርን ስታስብ መልካም የሆነው ነገር እንዳታጣ ይላል ሼክስፒር፡፡በመጀመርያው ስራህ ሙሉ ወይም ፍፁም ላይሆን ይችላል በመልካሙ ግን ልትጀምር ትችላለህ፡፡በገድል ላይ ሊያዘልሉ የሚችሉ ምርቶችንና ውጤቶችን ማምጣት ነው አሸናፊዎችንና ከተሸናፊዎች የሚለያቸው፡፡በቴክኖሎጂው አለም እውቅናን የሚያመጣው ዝቅተኛው አስፈላጊ እና ሊዳብር የሚችለው ምርት ነው፡፡ተመልከቱ ሁሉም ቴክኖሎጂ ሲጀምር እንዲህ የተራቀቀ አልነበረም፡፡ ኮፒውተር ለምሳሌ ቤት ያክል ነበር፡፡አሁን ላይ የእጅ ያክል ሆኗል፡፡ምን አልባት ኮመፒውተርን የፈጠረው ሰውዬ የእጅ እስኪያክል ቢጠብቅ ኖሮ ኮምፒወተርን እስከ አሁን ባለወቅነው ነበር፡፡ስለዚህም ባላችሁ ጀምሩ፡፡ምን ስራ ስሩ ትልቅ ለመሆን ስሩ፡፡የመጀመርያው ለመሆንም ታትሩ፡፡ከልምዳችሁ ተማሩ፡፡


















3.  ጠንካራ ሁኑ
የፈለጋችሁን ነገር መሆን ትችላላችሁ መጀመርያ ግን ጠንካራ ሀኑ ይለናል ፓቬል ታሱቱሌን
በስራ ቦታችሁ ሁሉን ሰዓት ማሳለፍ ያደነዝዛችኋል ስለዚህም እንቅስቃሴ አድርጉ ፡፡ይህም ከጭንቀት የሚገላግል ነው፡፡እረፍት ማድረግን መርሳት የለባችሁም፡፡
4.  ድንበር ማበጀት
ድንበር ማበጀት ማለት ለራሳችን ግምት መስጠት ማለት ነው፡፡ሌሎችንም የሚያስከፋ ቢሆን ማለት ነው፡፡ብዙ የሚሰሩ ስራዎች አሉ፡፡ስራዎችን ወይም ፕሮጀክትን ሳይጨርሱ በስራ መውጫ ሰዓት መውጣትን ይልመዱ፡፡በእርፈት ጊዜዎ ስለ ስራ አያስቡ፡፡ ኢሜይል እንኳን ቼክ አያድርጉ፡፡ጠንክረው ይስሩ በደንብ ይረፉ፡፡
5.  በጊዜ መነሳት
በጊዜ መተኛትና በጊዜ መነሳት ሰውን ጤናማ፣ሀብታምና ብልህ ያደርጋል፡፡ማታ ላይ እንቅልፍ ባይንህ የማይድር አይነት ሰው ልትሆን ትችላለህ፡፡ይህ ግድም አይስጥህ በጊዜ መተኛትን ለመልመድ ራስህን አሳምን፡፡በጊዜ መነሳትንም እንደዚያው፡፡11 ሰዓት ከእንቅልፋቸው የሚነሱ ግለሰቦችን ተቀላቀል አልያም 12 ሰዓት ለመነሳት ሞክር፡፡ይህም ማንም ጣልቃ ሳይገባብህ እቅድህን አውጥተህ ውጤታማ መሆን ትችላለህ፡፡ሰዎች ከተነሱ በኋላ የምታቅዳቸው እቅድች ሁሉ የተበረዙ ናቸው፡፡
6.  ስለገንዘብ ያለን እውቀት ማሳደግ
በስራህ መጀመርያ የገንዘብን እውቀት ማስተር ማድረግ አለብህ፡፡የገንዘብ ጨዋታን ማለት ነው፡፡አለበልዚያ በእድሜህ ማምሺያ ላይ የሚያጋጥም ምሬት ውስጥ ትገባለህ፡፡ስራዬን ትቼ በ18 አመቴ አለምን ለማሰስ የተነሳሁት የቁጠባና የኢንቨሰትምንትን ጥቅም በልጅነቴ በመረዳቴ ነው፡፡ቤተሰቦቼ ስደተኞች ናቸው፡፡የገንዝብን ክፋት ያዩሀት በልጅነቴ ነው፡፡ቤተሰቦቼ አጥተው ሲንከራተቱ ማለት ነው፡፡በአግባቡ ካልተጠቀምክበት ገንዘብ አጥፊህ ነው፡፡በአግባቡ ማውጣት መቆጠብ ኢንቨስት ማድረግ፡፡ ይህ የህይወትህ መርህ ይሁን፡፡የገንዘብ አወጣጥን በአግባቡ የተማረ ሰው ከስራው በ40 ዓመቱ ጡረታ እንኳን ቢወጣ ምንም አይሆንም፡፡
7.  ቁጣባ
በምትችለው አቅም ገና ወጣት እያለህ ለመቆጠብ ሞክር የምትችለውን ያክል፡፡አንድ ሰው ከሆነ ጊዜ በፊት ዛፍ ተክሎ ባይሆን ኖሮ ሌላው ፀሃይ ሲወጣ መጠለል አይችልም ነበር፡፡ከምታገኘው ገንዘብ ከፍተኛውን መጠን መቆጠብ ያለብህ በእድሜህ ኋላ ኋላ ላይ የፋይናንስ ነፃነት እንዲኖርህ ነው፡፡

8.  ወጪ
ለምተወዳችው ጥሩ ነገሮች በነፃነት ገንዘብ መድብ፡፡በምትወዳቸው ነገሮች ላይ ያለ ርህራሄ ገንዘብ አውጣ በማትወዳቸው ነገሮች ላይ ደግም ያለርህራሄ እጅህን ሰብስብ፡፡ልብስና ጫማ ላይ ሳይሆን ህልምህ ላይ ገንዘብህን አፍስስ፡፡አስተውል በሌሎች ነገሮች ላይ ሁሉ ቁጣባህ ይጠንክር፡፡
9.  እረፈት
በአመቱ መጨረሻ ከሚኖር መማረር የእረፍት ጊዜህን በእቅድ ተጠቀም፡፡ ያለ እረፈት መስራት አዕምሮን ማዛል ነው ትርፉ፡፡ስለዚህም የሚገባውን ያክል የእረፍት ጊዜ ይኑርህ፡፡
10.        ሆቢ
የራይት ወንድማማቾች አውሮፕላን የፈለሰፉት የቀን ተቀን ሳይክል ጥገና ስራ ስለሰለቻቸው ነው፡፡ስለዚህም ሆቢ ማዳበር ተገቢ ነው ዮጋ ሊሆን ይችላልበእግር ወክ ማድረግ አልያም መፅሃፍ ማንበብ አልያም ደግሞ ቼዝ መጫወት፡፡በእነዚህ ውስጥ ግን የራስህን ስራ ሰርተህ ለመውጣት መሞከር ይገባል፡፡

ተተርጉሞ የተጫነው በጥሩሰው ገረሱ

Comments

Post a Comment

Popular Posts