ደንበኞቻችን የሚወዱትን
ደንበኞቻችን የሚወዱትን
ፍቅር የሁሉም ነገር ማግኔት ነው፡፡በፍቅር የሚሰሩት ስራ ሁሌም ለስኬት ወሳኝነቱ የጎላ ነው፡፡ደንበኞችም
የሚወዱትን ስራ መስራት ወይም ምርት ማቅረብ የስኬት ማገርና መሰሶ ነው፡፡በዕድል አላምንም ዕድል በንግድ ስራ ውስጥ እምብዛም
ቦታ የለውም ምክንያቱም ዕድል ሊተነበይ የሚችል ሀይል አይደለምና ነው፡፡እጃችሁን አጣምራችሁ መልካሙን ብትመኙ ስራው ሊሰራ
አይችልም፡፡ስለዚህ ሊተነበይ የሚችለው የቱ ነው ጠንካራ ሰራተኛነት፣የአላማ ፅናት ሌላኛው ደግሞ ሊያስገርማችሁ ይችላል፡፡ይህ
ባህሪ ፍቅር የምንለው ነው፡፡አሁን አሁን በግልፅ እየታየኝ የመጣው የምንወደውን መስራት ለቢዝነስ ስኬት የትንበያ መሳርያ መሆኑ
ነው፡፡
|
|
|
|
|
|
ስኬታማ ቢዝነስ ለመገንባት ፍቅር ወሳኝ ነው፡፡ሰዎች ሊወዱት የሚችሉትን
ምርት ለማምረት ትኩረት ካደረግክ ስኬት ይከተልሃል፡፡የዚህ አይነት የቢዝነስ አካሄድ እድገትን፣ታማኝነትን፣የሰራተኛ የመቆየት
አቅምን እና ትራፋማነትን ያመጣል፡፡
ምናልባት ፍቅር በስራ ቦታዎ ላይ ምንም ቦታ እንደሌለው ያስቡ ይሆናል፡፡ከስራ ቦታዎ ባህል
የተነሳ ፍቅር በዚያ ቦታ ሊያድግ እንደማይችል ሊታሰብ ይችላል፡፡ቢዝነስ የሰዎች ግንኙነት ነው፡፡ስለዚህ ፍቅር ለምንሰራው ስራ
መሰረቱ ነው፡፡
እስኪ ለስኬት መተንበያ ብለን ወዳነሳነው ሀሳባችን እንመለስ፡፡ወደ ስኬትዎ በእድል ብቻ አልያም
ደግሞ የማይጨበጡ ህልሞችን በማለም መድረስ አይችሉም፡፡ወደ ስኬት ማምራት የሚቻለው ደንበኞች የሚወዱትን ምርት በማምረትና
ሰራተኞችም ለመስራት የሚወዱትን በማሰራት ነው፡፡
ረዥም ጊዜ የሚዘልቅ እሴትን መገንባት ላይ ትኩረት ስናደርግ ልንኮራበት የምንችለውን ነገር
መገንባት እንችላለን፡፡ራዕይ የመኖርና በፅናትና በታታሪነት የመድረስ ጉዳይ ነው፡፡
ይህ
እንዴት ማሳካት ይቻላል
ደንበኞች የሚወዱትን ችግሮቻቸውን የሚፈታ እና ህይወታቸውን የሚያሻሽል ምርት ማምረት፡፡ለደንበኞች
ያልዎትን ፍቅር ሁሌም ምርትዎን በማሻሻል ማሳየት፣ለፍላጎታቸውን ማድመጥና ለዚያም ምላሽ መስጠት፣የሚያስደንቃቸውንና
የሚያስደስታቸውን ማሳሳያዎች ማቅረብ.ችግሮች ሲከሰቱ በፍጥነት እና የፊት ለፊት ምላሽ መስጠት፡፡
ይህ
እንዴት ለስኬት ይረዳል
·
ምክንያቱም ትክክለኛ ፍላጎትን ለማሳካት እየሰራችሁ
ስለሆነና ደንበኞች ትርጉም ያው አንድ ነገር እንዲያሳኩ ስለሚረዳ፡፡
·
ተከታታይነት ያለው የደንበኞች ጋር ግንኙነት ድንበኞችን
በቀጣነትም ሊያረካቸው እንደሚችል ማስተማመኛ ስለሚፈጥር፡፡
·
ይህም ምርቱንና ድርጅቱን እንዲወዱትና እንዲያምኑት
ስለሚያደርግ ከዚህ ባሻገር ሌሎች ምርቱን እንዲጠቀሙ ሊያግባቡ ስለሚችሉ
·
የሁለትዮሽ የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነትን ስለሚፈጥር
ሰራተኞችን መውደድ





እንዲህ አይነት አርዓያነት የተሞላበት አካሄድ ቀጣይነት ያለው እድገትና ደስታን ይፈጥራል፡፡ሰራተኞች
ስራቸው ውጤታማ የሆነና እያደገ መሆኑን እንዲሁም የሚያከብሩትና የሚከበሩበት መሆን ይረዳሉ፡፡
ያለፍቅር የረዥም ጊዜ ስኬት ይርቃል፡፡ምን ያክል ገንዘብ በባንክ ይኑሮት ምንም ያክል ጠንካራ
ሆነው ይስሩ፡፡
http://www.cnbc.com/2017/03/31/love-is-the-greatest-predictor-of-business-success.html
Comments
Post a Comment