ማንሳ ሙሳ፡የአለማችን የምንግዜም ሀብታም
ማንሳ ሙሳ፡የአለማችን የምንግዜም
ሀብታም
ስለአለማችን
የምንግዜም ሀብታም ስነስብ ወደ አዕምሮአችን ቀድሞ የሚመጣው ስም ቢልጌትስ ዋረንቡፌት ወይም ጆን ዲ ሮክፌለር የሚለው
ነው፡፡ነገር ግን ስለ አስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ሚስጢር አፍሪካዊው
ንጉስ ማንሳ ሙሳ ጥቂቶች ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡አለማችን እስከ
አሁን ድርስ ካየቻቸው ባለሀብቶች መካከል ቀዳሚ የሆነው ግሰለብ ማንሳ ሙሳ ማሳ ሙሳ የታሪካዊቷ ማሊ ግዛት ንጉስ የነበረ ሲሆን ሀብቱም 400 ቢሊየን ዶላር እንደነበር ይገመታል፡፡
አስረኛው
የማሊ ማንሳ የሆነው ማንሳ ሙሳ ኢሚር ኦፍ ሜሌ ሎርድ ፈ ማይንስ ኦፍ ዋንጋራ እና ኮንከረር ኦፍ ጋንታ ፉታ ጃሎን በሚሊ
ስሞቹም ይታወቃል፡፡፡ንገሱስ ሙሳ የምዕራባዊቷ አፍሪካዊ ሀገር
የሆነችውን ማሊ በ13 00 ክፍለ ዘመን የመራ ንጉስ ነው፡፡እስከ አሁን ድርስ ቆመው ያሉትን የማሊን የስልጣኔ ማሳያዎችም
የገነባው ይህ ንጉስ ግዛቶቹን ሲያስተዳድር ዋነኛ የሀብቱ ምንጩ የሀገሪቱ ወርቅ ነበር፡፡
በ1312 ወደ ስላጣን የመጣው ሙሳ ኬታ ንግስናውን ሲየገኝም
ማንሳ ወይም ደግሞ ንጉስ የሚል የክብር ስሙን ተጎናፅፏል፡፡ወቅቱ ብዙ የአውሮፓ ሀገራት በጦር የሚተራመሱበት የነበረ ሲሆን
አብዛኛው የአፍሪካ ሀገራት ግን በእድገት የተነበሻበሹበት ወቅት እንደበርም ይገለፃል፡፡
የግዛቱም ስፋት 2000 ማይል ይሸፍን ነበር፡፡ይህም በአሁኑ
ወቅት ሞሪታንያ፣ጋምቢያ፣ጊዚ፣ቡርኪናፋሶ፣ማሊ፣ኒጀር፣ናይጄሪያና ቻድን ሁሉ ግዛቱ ይሸፍን ነበር
አለም ከማንሳ ሙሳ ሀብት ጋር የተዋወቀችው ማሳ ሙሳ በ1324 ከማሊ ተነስቶ 4000
ማይል አቋርጦ ወደ መካ ባደረገው ጉዞ ነበር፡፡ከማሊ እስከ ገብፅ ክግብፅ እስከ ሳውዲ አረቢያ ድርስ በሀብት ሙላት የተደረገ
ውዱ የአለማችን ጉዞ፡፡ሙሳ ሀብቱን በደረሰበት እያካፈለ ብዙዎችንም እያንበሻበሸ አንዳንድ ከተሞችንም እየለወጠ ያደረገው ጉዞ እንደነበርም
አብረውት የተጓዙት የታሪክ ፃፊዎች የከተቡት ፅሁፍ ይገልፃል፡፡ይህን ጉዞ ሲያደርግ ማንሳ ሙሳ በአለማችን ላይ ከአንድ ቦታ ወደ
አንድ ቦታ ንጉሶች ካደረጉት ጉዞ እጅግ የተለየና አለማችን እስከ አሁንም ደረስ ያላየቸውን አይነት የሀብት ችሮታ
ያስተናገደችበት ጉዞ እነደነበር ይገለፃል፡፡አይን ሊያይ እስከሚችልበት ጫፍ ደረስ የተዘረጋ 60 ሺ ተዋጊ ጦር ፣በ12 000 አገልጋይ
ባሮች፣እያንዳንዳቸው 1.8 ኪሎግራም ወርቅ የያዙ 5000 ጃንደረባዎችን ያሳተፈው የማንሳ ሙሳ ጉዞን አለማችን በድንቅ መዝገቧ
ከትባዋለች፡፡
የማንሳ ሙሳ ጉዞ በጉዞው ወቅት ለረፈባቸው አከባቢዎች ብዙ ለውጥን ያመጣ ነበር፡፡በጉዞው
ውስጥ ከሚነሱት አስገራሚ ጉዳዮች መካከል በግብፅ ካይሮ ባረፈበት ያደረገው ይነሳል፡፡በወቅቱ የግብፃ ካይሮ በታሪኳ አይታ
የማታውቀውን ያክል ወርቅና ገንዘብ ይዛ አድራለች ነዋሪዎቿም ካጣና የነጣ ኑሮዋቸው በማንሳ ሙሳ ችሮታ ተንበሽብሸዋል፡፡ ብዙ
ወርቆችንና ብሮችን ለድሆች የቸረ ሲሆን በዚህም የገንዘብ ጎርፍ የተጥለቀለችው ካይሮ ይህ የሀብት ሱናሚ በኑሮ ላይ ካስከተለው
ግሽበት ያገገመችው ከአመታት በኋላ እንደነበርም ይወሳል፡፡ ይህ አስደናቂ ጉዞ ማነሳ ሙሳ በአለም ካርታ ላይ አሻራውን
ያሰረፈበት ግዙፉ ጉዞ እንደበረም የታሪክ ምሁራን ፅፈዋል፡፡
ማንሳ ሙሳ ሀብት ላይ ብቻ ያተኮረ ንጉስ እነደልነበር ይገለፃል፡፡በተለይም የሚያስተዳድራቸውን
ግዛቶች በእውቀት በማደርጀቱና ከዘመናዊ ስልጣኔ ጋር በመስተዋወቁ ረገድ ስሙ በብዙዎች ይነሳል፡፡ከሌሎች የአለማችን ክፍሎች
በማምጣት ቲመቡከቱን ጨምሮ ሌሎች የግዛቱን ክፍሎች ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉባቸው ብሎም እውቀት የሚተላለፍባቸው የወቅቱን
ግዙፍ መማርያዎችን ገንብቷል፡፡ከተሞችንም አስፋፍቷል፡፡
ከመካ
ጉዞው ሲመለስም ማንሳ ሙሳ በአረቡ አለም የተመለከታቸውን ስልጣኔዎች ወደ ሀገሩ በማምጣት አስተዋውቋል፡፡ የአረብ
ምሁራንን፣አስተዳደሪዎችንን የግናባታ ባለሙያዎችን በተለይም የወቅቱ እውቅ አርኪቴክቸር የነበረውን ኢሻቅ ኢልታጁኒን ወደ ግዛቱ ይዞ በመምጣት በማሊ አስደናቂ የአርኪቴክቸር
ስራዎችን አስገንብቷል ስልጣኔንም አስተዋውቋል፡፡
በ1280
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የተወለደው የአለማችን የምንጊዜም ሀበታም ማንሳ ሙሳ በ1337 እስከሞተበት እለት ደርስ 400 ቢሊየን
የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ሀብትን አካብቷል፡፡ለ25 ዓመታት 2000 ማይል የሚሸፍን ግዛት ካስተዳደረ በኋላ በ1337 ሲሞት
ልጁ ማጋን አንደኛ ተክቶታል፡፡
በጥሩሰው
ገረሱ
Yes
ReplyDelete