የሩቅ ምስራቋ ፈርጥ፡-ማሌዢያ

በጥሩሰው ገረሱ
በደቡብ ቻይና ባህር ለሁለት እኩል ግዛቶች የተከፈለችና 330 ሺህ ስኬዌር ማይል የምትሽፍን ፣አስራ ሶስት ክልሎችና ሶስት የፌደራል ግዛቶች ያሏት ሀገር፡፡ከታይላንድ ጋር የውሃና የደረቅ መሬት ስትዋሰን ከሲንጋፖር፣ቬትናምና ኢንዶኔዢያ ጋር ደግሞ የውሃ ክልል ትዋሰናለች፡፡የሀገሪቱ ዋና ከተማ ኩዋላ ላምፑር ስትሆን ፑትራጃ የፌደራሉ መንግስት መቀመጫ ነች፡፡ሰላሳ ሁለት ሚሊየን ህዝብ የሚኖርባት የዛሬዋ መዋዕለ ንዋይ ኢኮኖሚ ቅኝት ሀገር ማሌዢያ፡፡
ማሊዢያ ምስረታዋን ከማሌ ስረወ መንግስት መነሻ ስታደርግ በ18ው ክፍለዘመን በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር ወድቃ የነበረች ሀገር ነች፡፡ከግማሽ በላይ የሚሆነው ህዝቧም የማሌ ህዝብ ነው፡፡
ማሌዢያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ያሳየችው በ20 ክፍለዘምን ሲሆን የሀገሪቱ ህዝብ አማካይ አመታዊ ገቢም 11 ሺህ ስለሳ ሁለት ዶላር እንዲሁም የሀገሪቱ አጠቃላይ አማካይ አመታዊ ምርት 383 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፡፡እንደ ኤችኤስ ቢሲ የ2012 ዘገባ ማሌዢያ የአለማችን ሀያ አንደኛ ኢኮኖሚ መሆን ችላለች፡፡የ1997 የኢሲያ አህጉር የፋይናንስ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት የሀገሪቱ መገበያ ገንዘብ መሌዢያን ሪንጅት በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘ የመገበያያ ገንዘብ እስከመሆን ደርሶ የነበረ ሲሆን አንድ ዶላር 2.5 የሀገሪቱ ብር ሆኖ በወቅቱ ይመነዘር ነበር፡፡ እስከ ግንቦት 2017 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠርም አንድ የማሌዢያ ገንዘብ በ4.32 ሪንጂት ተመንዝሯል፡፡
ማሌዢያ በተፈጥሮ ሀብት እጅግ የታደለች ሀገር ነች፡፡በተለይ በግብርና፣ደንና የተፈጥሮ ማዕደናት፡፡ሀገሪቱ ኤክስሰፖርት ከምታደርጋቸው ምርቶች አሌክትሮኒክስና ነዳጅ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ከዚህ ባሻገርም ማሌዢያ የአለማችን ቁጥር አንድ የተፈጥሮ ጎማ እና ፓልም ዘይት የምታምርት ሀገር ነች፡፡የሀገሪቱ የግብርና ምርት ከሆኑት መካከልም ካካዋ፣ቁንዶ በርበሬና አናናስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡እሰክ 2011 ባለው ጊዜ የሀገሪቱ የሚታረስ መሬት 5.44 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ከዚህም ውስጥ በሰብል የተሸፈነ መሬት 17.49 በመቶ ይደርሳል፡፡በመስኖ የሚለማው የሀገሪቱ የመሬት ይዞታም 3800 ስከዌር ኪሎሜትር የሚሸፍን ሲሆን ቲንና የተፈጥሮ ነዳጅ ዘይት በማሌዢያ ኢኮኖሚ ውስጥ ግዙፍ ድርሻ ይዘው የመጡና ተለይም በአንድ ወቅትም ማሌዢያ የአለማችን ቁጥር አንድ ቲን አምራች የነበረችብት ሂደት ተመዝግቧል፡፡ይህም የአለም አቀፍ ምርቱን 31 በመቶ የሚሸፍን ነበር፡፡

በ1972 የነዳጅ ዘይት ምርት የሀገሪቱ ትልቁ የገቢ ምንጭ እስከሆነበት ወቅት ደረስ የቲን ምርት ከፍተኛው የኢኮኖሚ ድርሻን ይሸፍን ነበር፡፡በሌላ በኩልም ካኦሊን፣ሲልካ፣ላይምስቶን፣ባራይት እና ፎስፌት በሀገሪቱ የሚገኙ ማዕድናት ናቸው፡፡በተወሰነ ደረጃም ወርቅ በሀገሪቱ ይመረታል፡፡
እስከ 2014 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ማሌዢያ 4 ቢሊየን በርሜል የሚጠጋ ድፍድፍ የነዳጅ ሀብት እንዳላት በጥናት የተረጋጋጠ ሲሆን ይህም ከቻይና ህንድና ቬትናም ቀጥሎ በኢሲያ አህጉር አራታኛው ትልቁ መጠን ነው፡፡ከዚህ ባሻገርም ማሌዢያ የ83 ትሪሊየን ኪውቢክ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አላት፡፡በ2015 የማሌዢያ ኢኮኖሚ ተወዳደሪነት እጅግ ያደገ ሲሆን በአለማችንም 14 አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡በ2016 የአለም ባንክ ባወጣው መረጃ መሰረት ማሌዢያ ቢዝነስ ለመስራት ምች ከሆኑ ሀገራት መካከል 18 ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን በኢሲያም ሲንጋፖርን ተከትላ ሁለተኛ ደረጃን አግኝታለች፡፡የፎሬን ሊስ መፅሄት በ2015 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ባወጣው መረጃ መሰረት ማሌዢያ የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳቡ በኩል 5 ደረጃን አግኝታለች፡፡
በ2016 የማሌዢያ የወጪ ንግድ 189 ቢሊየን የደረሰ ሲሆን ማሌዢያ የአለማችን 21 ግዙፍ ኤክሰፖርትር እንዲሁም በገቢ ንግድ ደግሞ 25 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡የማሌዢያ ዋነኛ የንግድ ሸሪክ ቻይና ስትሆን የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውወጥ 106 ቢሊየን ዶላርም ደርሷል፡፡የማሌዢያ ሁለተኛዋ የንግድ አጋር ሲንጋፖር ስትሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ግንኙነት መጠን 91 ቢሊየን ዶላር ይደርሳል፡፡ይህም በኢሲያ ሀገራት መካከል የሚደረገው የንግድ ግንኙነት 12 በመቶ ያክሉ ነው፡፡ማሌዢያ ከጃፓንም ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት በተከታይነት የሚጠቀስ ነው 42 ቢሊየን ዶላር ይጠጋል፡፡
ማሌዢያ የአሜሪካን የንግድ ሸሪክም ስትሆን በ1999 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የጀመረው የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የንግድ አጋርነት 30 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን አሜሪካን ወደ ማሌዢያ ኤክሰፖርት የምታደርገው መጠንም 9.1 ቢሊየን ይጠጋል፡፡ማሌዢያ ወደ አሜሪካን የምትልከው የወጪ ንግድ መጠንም 21.4 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፡፡
በአንድ ወቅት የማሌዢያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የነበረው ግብርና በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት መጠን 7.1 በመቶ ብቻ ይሸፍናል፡፡በግብርናው ዘርፍም ህይወቱን የሚመራው የሰራተኛ ቁጥርም ከ11 በመቶ የዘለለ አይደለም፡፡በ1960 ግብርና የሀገሪቱን አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት 37 በመቶ ይሸፍን የነበረ ሲሆን ለስራ የደረሰውም የሀገሪቱ ህዝብ 66 በመቶ ያክሉ በዚህ ዘርፍ ላይ ተሰማርቶ የሚሰራ ነበር፡፡ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ግብርና ለኢኮኖሚው የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ዝቅተኛ ቢሆንም ማሌዢያ የፓልም ዘይት በማምረት በአለማችን ሁለተኛዋ ሀገር ነች፡፡ኢንዶኒዢያ ብዛት ያለው የፓልም ምርት በማመረት ቀዳሚ ብትሆንም በ5 ሚሊየን ሄክታር ላይ ፓልምን የምታለማው ማሌዢያ በፓልም ኤክስፖርት ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች፡፡በአመት ማሌዢያ 18 ሚሊየን ቶን ፓልም ዘይት ኤክስፖርትም ታደርጋለች፡፡
የማሌዢያ የኢንዱስትሪው ዘርፍ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከአንደ ሶስተኛ በላይ ይሸፍናል፡፡በኢንዱስትሪው ዘርፍም ከአጠቃላይ ሰራተኛ ሀይሉ ውስጥ 36 በመቶ የሰራተኛ ሀይል የሚይዘው ይኸው ዘርፍ ነው፡፡በዘርፉ የኤሌክትሮኒክስ፣የአውቶሞቲቭ እና የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙ ናቸው፡፡የኤሌክትሪክና አሌክትሮኒክስ ዘርፉ በማሌዢያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ሲሆን ሀገሪቱ ኤክስፖርት ከምታደርጋቸውም ምርቶች 32 በመቶውን የሚሸፍነው ይኸው ዘርፍ ነው፡፡ ከሀገሪቱ የሰራተኛ ሀይልም 27.2 በመቶው ተቀጥሮ የሚሰራው በዚህ ዘርፍ ነው፡፡በዚህ የኢንዱስትሪ ክፍል ውስጥ የሞባይል ታብሌቶች፣ኦፕቲካል ፋይበር፣ኤል ኢዲ ቴሌቪዥኖች እና ኢንተግሬትድ ሰርኪውቶች በስፋት ይመረታሉ፡፡ማሌዢያ በፀሃይ ብርሃን የሚሰሩ እቃዎች አምራችንትንም ትመራለች፡፡
በኢንዱሰትሪው ውስጥ ሌላው ተጠቃሽ ክፍል የመኪና አምራች ዘርፉ ነው፡፡በማሌዢያ 27 ያክል መኪና አምራች ድርጅቶች ሲኖሩ 640 ያክል ደግሞ የመኪና ክፍሎችን የሚያርመርቱ ድርጅቶች ይገኛሉ፡፡ኢንዱስሰትሪው በኢሲያ አህጉር በሶስተኛ ደረጃ ያለ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በአመት 500 መቶ ሺህ መኪኖችን በማምረት በ23 ደረጃ ላይ የተቀመጠ ነው፡፡ይህ ዘርፍ ለኢኮኖሚው የ4 በመቶ ድርሻን የሚያበረክት ሲሆን በስሩም ከ700 መቶ ሺኅ በላይ ሰራተኞችን ይዟል፡፡
የማሌዢያ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አጠቃላይ የኢኮኖሚ አቅም መጠን 32 ቢሊየን ዶላር ደርሷል፡፡በዚህ የግንባታ ዘርፍ ውስጥ ለመኖርያነት የሚገለግሉ ህንፃዎች ግንባታ 29.7 በመቶ፣ለተለያዩ የንግድና ሌሎች ዘርፎች የሚገለግሉ ህንፃዎች ግንባታ 34.6 በመቶ እንዲሁም የመንገድ ግንባታ 30.6 በመቶውን ይሸፍናል፡፡
ማሌዢያ በፋይናንስ ዘርፍ በአለማችን ላይ ካሉ ሀገራት 22 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ 27 የንግድ ባንኮች፣15 የኢንቨስትመንት ባንኮች እና 2 ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የቱሪዝም ዘርፍ ሌላው የማሌዢያ ኢኮኖሚ አጋዥ ሀይል ነው፡፡ዘርፍ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥም 57 ሚሊየን የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች እንዲሁም 25 ሚሊየን የውጪ ቱሪስቶችን በመሳብ 30 ቢሊየን ዶላር ገቢ አስገኝቷል፡፡እንደ አለም የቱሪስት ድርጅት መረጃ ማሌዢያ በአለማችን ላይ ካሉ የቱሪስት መዳረሻ ከተሞች 10 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡የማሌዢያ ዋናዋና የቱሪስት መዳረሻዎች ሙሉ ዋሻ፣ፐርህኒቲያን ደሴቶች፣ላንጋካዊ፣ፔትሮናስ ታወር እና የኪናባሉ ተራራ ናቸው፡፡የህክምና ቱሪዝም የሀገሪቱ ሌላው የገቢ አመንጪ ዘርፍ ሲሆን በየአመቱ 1 ሚሊየን ሰዎች ለህክምና ወደ ማሌዢያ ይጓዛሉ፡፡ይህም ለኢኮኖሚው በአንድ አመት ከ200 ሚሊየን ላር በላይ ገቢ የሚያስገኝ ነው፡፡
ማሌዢያ እየተነቃቃ የሚገኝ የነዳጅ ምርት ዘርፍም አላት፡፡የሀገሪቱ የነዳጅ አምራች ድርጅት ፔትሮናስ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ በማስገኘት በአለማችን ላይ ካሉ 69 ግዙፍ የነዳጅ አምራች ድርጅቶች መካከል ተመድቧል፡፡ፔትሮናስ የማሌዢያን ኢኮኖሚ 37 በመቶ ገቢም ያስገባል፡፡ሀገሪቱ ካላት የነዳጅ ክምችት ቦታዎችም 40 በመቶ ያክሉ እየለማ የሚገኝ ሲሆንበዚህ ዘርፍም ከ3500 በላይ ድርጅቶች እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የማሌዢያ መሰረተ ልማት በከፍተኛ ደረጃ ካደጉ ሀገራት ተርታ የሚመደብ ነው፡፡4.7 ሚሊየን የቀጥታ መስመር የስልክ ተጠቃሚዎችን እንዲሁም ከ40 ሚሊየን በላይ የሞባይል መስመር ተጠቃሚዎችን የሚያስተናግድ የቴሌኮሙኒኬሽ መሰረተ ልማት፣7 አለም አቀፍ ደረጃቸው የጠበቁ ወደቦች፣200 የኢንዱሰትሪ ፓርኮች በሀገሪቱ ይገኛሉ፡፡
የማሌዢያ የሀይል አቅም ከ29,728 ሜጋ ዋት በላይ ሲሆን ሀገሪቱ በሰዓት የምታመርተው የሀይል መጠን 140 985 ጊጋዋት እንዲሁም በሰዓት የሀገሪቱ አጠቃላይ የሀይል ፍጆታ ደግሞ 116 ሺህ 87 ጊጋዋት ይደርሳል፡፡
በኢሲያ አህጉር በዘመናዊ የመንገድ ስራዎች ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትሰለፈው ማሌዢያ 144,403 ኪሎሜትር የሚሸፍን የመንገድ ግንባታ አከናውናለች፡፡1798 ኪሎሜትር የሚሸፍን ዘመናዊ ሀይዌይ፣1833 ኪሎሜትር የሚሸፍን የባቡር መንገድ እና 118 የአየር ማረፍያ ገንብታለች፡፡
የማሌዢያ ኢኮኖሚ በ2017 እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ ሰኔ ደርስ ባለው ጊዜ የ5.8 በመቶ እድገት ያስመዘገበ ሲሆን ይኼም ከ2015 እስከ አሁን ደረስ ባለው ሂደት ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡የሀገሪቱን እድገት አስመልክቶ የስነምጣኔ ምሁራን 5.4 በመቶ እንደሚያድግ የተነበዩ ሲሆን በሰኔ ወር የተመዘገበው ግን ከትንበያው የ0.4 በመቶ ጭማሪን ያሳየ ነው፡፡በያዝነው ዓመት የሀገሪቱ የሰርቪስ ዘርፍ የ6.3 በመቶ እድገት ሲያሳይ፣የፋይናንስና ኢንሹራንስ ዘርፉ የ8.5 በመቶ እንዲሁም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የ6 በመቶ እድገት አስመዘግቧል፡፡የሀገሪቱ የወጪ ንግድ በ9.8 በመቶ ያደገ ሲሆን የገቢ ንግዱ እድገት ደግሞ 10.7 በመቶ ሆኖ ተመዝገቧል፡፡የማሌዢያ አጠቃላይ ሀገራዊ ሀብት መጠን  $863.8ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን 32 ሚሊየን የሚጠጋው የሀገሪቱ ህዝብ አማካይ አመታዊ ገቢው በግለሰብ ደረጃ 26,315 ዶላር ደርሷል፡፡ባለፉት ሶስት አስር አመታት ማሌዢያ ድህነትን በማሰወገድ መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሀገራት ተርታ መሰለፍ የቻለች ሲሆን እስከ 2030 ባሉት አመታትም ሀገሪቱ ወደ አደጉት ሀገራት ተርታ እነደምተሰለፍም የስነምጣኑ ባለሙያዎች ተንብየዋል፡፡በአንድ ወቅት ዜጓቿን መመገብ ተስኗት የነበረችው ማሌዢያ 40 በመቶ የሚደርሰው ከድህነት ወለል በታች ሆኖ ይኖር የነበረው ህዝቧን ወደ መካከለኛ ገቢ ማሳደግ ችላለች፡፡

                            


Comments

Post a Comment

Popular Posts