የኢሲያ አህጉር የአለምን ኢኮኖሚ እድገትን እስከ 2030 ይመራል
የአለም አቀፉ ኢኮኖሚ ከደረሰበት የፋይናንስ ቀውስ መጠነኛ
ማገገም እያሳየ ይገኛል፡፡የኢሲያ አህጉር ሀገራትም እስከ 2030 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ተከታታይ ፈጣን እድገት
የሚያስመዘግቡ ሀገራት ተርታን ይመራሉ፡፡ቻይናና ህንድ ደግሞ ይህን ፈጣን እድገት እያስመዘገበ የሚቀጥለውን የኢሲያ ኢኮኖሚ
በአንደኝነትና ሁለተኝት ይመሩታል፡፡የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብርብርና ልማት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው የኢኮኖሚ እድገቱ
በፈጣን ሁኔታ እያደገ የመጣው ኢሲያ አህጉር ኢንቨስትመንት፣በሀገራቱ የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና የገንዘብ ማነቃቂያዎች
በአብዛኞቹ ፈጣን እድገት በሚያስመዘግቡ ሀገራት የኢኮኖሚ እድግ ፈጣንና ተከታታይ መሆን በምክንያነት የሚጠቀስ ነው፡፡
ፓሪስ መቀመጫውን ያደረገው ይኸው ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት
የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ እድገት በ3.6 በመቶ ይቀጥላል፡፡በ2018 ይህ አሃዝ ወደ 3.7 በመቶ እንደሚያድግም ይጠበቃል፡፡ይህ
እድግት ይኑር እንጂ አለምን ከጋጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ በፊት ከነበረው ዝቅተኛ ነው እየተባለም ይገኛል፡፡ይመሩታል፡፡እንደ አለም
አቀፉ የኢኮኖሚ ትብርብርና ልማት ድርጅት መረጃ አለም ያስመዘገበችው እድገት ዝቅተኛ ይሁን እንጂ የኢሲያ ፓሲፊክ ሀገራት ከሰሃራ
በታች ያሉ ሀገራት አበረታች የኢኮኖሚ እድግት አስመዘግበዋል፡፡፡፡ቻይና ይህን ዓመት በ6.8 በመቶ እድገት የምታጠናቀቅ ሲሆን
ከቀናት በኋላ በምንቀበለው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመትም ቻይና የ6.6 በመቶ እንዲሁም በቀጣይ የ2019 የፈንርጆቹ ዓመት 6.4
በመቶ እድገት ታስመዘግባለች፡፡
የአለማችን ሶስተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ጃፓን የ1.5
አማካይ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት መጠን እድገት የምታስመዘግብ ሲሆን በቀጣይ ተከታታይ ዓመታትም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ1 በመቶ
የሚያድግ እንደሆነ ድርጅቱ ጠቁሟል፡፡
ደቡብ ኮርያ እስከ 2019 የአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በአለም
አቀፍ የንግድ እድገትና በሀገሪቱ መንግስት የኢኮኖሚ የበጀት ፖሊሰ ማሻሻያና የገንዘብ ድጋፍ በመታገዝ የ3 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብም
ተገልጻል፡፡
በአለማችን ላይ ላለፉት ሁለት አስርት ዓማት አስደናቂ የኢኮኖሚ
አድገት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ህንድ ደግሞ በያዝነው ዓመት የ6.7 በመቶ እድገት አስመዘግባ
የምታጠናቅቅ ሲሆን በ2018 የ7 በመቶና በ2019 የ7.4 በመቶ እድገትን ታስመዘግባለች፡፡እያደገ የመጣው የኢንቨስትምንት
መጠንና ምርታመነት የሀገሪቱን እድገት በከፍተኛ ደረጃም እንደሚደግፍ ተገልጿል፡፡
ኢንዶኒዢያም የተረጋጋ የኢኮኖሚ እድገት እንደምታስመዘግብ
የተገለፀ ሲሆን ሀገሪቱ የዜጎች ገቢ ከመጨመሩ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ የመግዛት እድገትና ለአገለግሎት ዘርፉ መነቃቃት መፍጠሩ
የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በ5 በመቶ እያሳደገው ይቀጥላል፡፡
የቤቶች ልማት ዝርፉ ከፍተኛ የእዳ ጫና ቢኖርበትም
የአውስትራሊያ ኢኮኖሚም በዚህ ዓመት የ2.5 በመቶ እንዲሁም በቀጣይ ዓመት የ2.7 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብም ተተንብይዋልል፡:በውጪ
ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የተነቃቃችው አጎራባች ኒውዚላንድም ከ3 በመቶ በላይ እድገት በ2018 እና 2019 የአውሮፓውያን አመት
እንደምታስመዘግብ የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብርብርና ልማት ድርጅት ያወጣው መረጃ ያመልክታል፡፡
የአለም አቀፉ ኢኮኖሚ ከደረሰበት የፋይናንስ ቀውስ የማገገሚያ
አመቱም የሚጨምር እንደሆነ የገለፀው ድርጅቱ የግሉ ዘርፍ፣ኢንቨስትመንት፣ምርታማነትና ንግድ ላይ ያሉ ግንኙነቶች በተወሰነ ደረጃ
መቀዛቀዝ ለአጠቃላይ እድገቱ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነው፡፡በአሁኑ ወቅት የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሰዎች ቁጥር ከቀውሱ በፊት
ከነበረው ከፍ ያለ ሲሆን ሰራተኛውም የሚያገኘው ገቢ የሚያድግ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብርብርና ልማት ድርጅት ባወጣው ዘገባ
መሰረት የአደጉት ሀገራት ቀስ በቀስ እያገገሙ እንደሚሄዱ የገለፀ ሲሆን የኢሲያ አህጉር ሀገራት በኢኮኖሚ እድገቱ የአለማችንን
ደረጃ ተቆጣጠረው እስከ 2030 ይዘልቃሉ፡፡የኢሲያ አህጉርም በ2030 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የአለማችን 40 በመቶ ሀብት
መጠን ኢኮኖሚ አቅም ይኖረዋል፡፡የዚህ ኢኮኖሚ እድግት ሚሰትጥርም በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት እድገት፣የኢንቨስትመንት
ምቹነት፣የንግድ ግንኙነት መጠናከርና የመንግስታት የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የኢሲያ ብርሃኖች ሲል ሪፖርቱ ያሞካሻቸው ሀገራት
ህንድ፣ቬትናምና ፊሊፒንስ ሲሆኑ ህንድ እስከ 2030 ባለው ጊዜ የአማካይ የ7 በመቶ እድገት እንዲሁም ቬትናምና ፊሊፒንስ የ6
በመቶ አማካይ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘግባሉ፡፡በኢሲያ አህጉር የህዝብ ቁጥሩ በ15 በመቶ እየጨመረ የሚሄድ ሲሆን ጃፓንንና
ቻይና እያረጀ የሚሄደው የህዝብ ቁጥራቸው ለኢኮኖሚ እድገታቸው ስጋት ሲሆን በሌሎቹ የኢሲያ ሀገራት የወጣት ሃይል ቁጥር መጨመር
ለተከታታይ የኢኮኖሚ እድግት እምቅ ሀይል ይሆናል፡፡የከተሞች መስፋፋትም በኢሲያ ሀገራት እስከ 2030 እንደ አውሮፓውያኑ
አቆጣጠር በ50 በመቶ እንደሚጨምርም ተተንቧል፡፡፡
Comments
Post a Comment