የኢሲያ አህጉር የአለምን ኢኮኖሚ እድገትን እስከ 2030 ይመራል
የአለም አቀፉ ኢኮኖሚ ከደረሰበት የፋይናንስ ቀውስ መጠነኛ ማገገም እያሳየ ይገኛል፡፡የኢሲያ አህጉር ሀገራትም እስከ 2030 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ተከታታይ ፈጣን እድገት የሚያስመዘግቡ ሀገራት ተርታን ይመራሉ፡፡ቻይናና ህንድ ደግሞ ይህን ፈጣን እድገት እያስመዘገበ የሚቀጥለውን የኢሲያ ኢኮኖሚ በአንደኝነትና ሁለተኝት ይመሩታል፡፡የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብርብርና ልማት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው የኢኮኖሚ እድገቱ በፈጣን ሁኔታ እያደገ የመጣው ኢሲያ አህጉር ኢንቨስትመንት፣በሀገራቱ የተደረጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና የገንዘብ ማነቃቂያዎች በአብዛኞቹ ፈጣን እድገት በሚያስመዘግቡ ሀገራት የኢኮኖሚ እድግ ፈጣንና ተከታታይ መሆን በምክንያነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ፓሪስ መቀመጫውን ያደረገው ይኸው ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት የአለም አቀፉ የኢኮኖሚ እድገት በ3.6 በመቶ ይቀጥላል፡፡በ2018 ይህ አሃዝ ወደ 3.7 በመቶ እንደሚያድግም ይጠበቃል፡፡ይህ እድግት ይኑር እንጂ አለምን ከጋጠማት የኢኮኖሚ ቀውስ በፊት ከነበረው ዝቅተኛ ነው እየተባለም ይገኛል፡፡ይመሩታል፡፡እንደ አለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብርብርና ልማት ድርጅት መረጃ አለም ያስመዘገበችው እድገት ዝቅተኛ ይሁን እንጂ የኢሲያ ፓሲፊክ ሀገራት ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት አበረታች የኢኮኖሚ እድግት አስመዘግበዋል፡፡፡፡ቻይና ይህን ዓመት በ6.8 በመቶ እድገት የምታጠናቀቅ ሲሆን ከቀናት በኋላ በምንቀበለው የፈረንጆቹ አዲስ ዓመትም ቻይና የ6.6 በመቶ እንዲሁም በቀጣይ የ2019 የፈንርጆቹ ዓመት 6.4 በመቶ እድገት ታስመዘግባለች፡፡ የአለማችን ሶስተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ የሆነችው ጃፓን የ1.5 አማካይ አጠቃላይ ሀገራዊ ምርት መጠን እድገት የምታስመዘግብ ሲሆን በቀጣይ ተከታታይ ዓመታትም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ1 በመቶ የሚያድግ እ...